The Hidden Words
Amharic · Bahá'u'lláh
Arabic Hidden Words BH00386
የመንፈስ ልጅ ሆይ!
የመጀመሪያ ምክሬ ይህ ነው:- ጥንታዊው፣ የማ ይጠፋውና ዘለዓለማዊው ልዕልና ያንተ ይሆን ዘንድ፣ ንጹህ፣ ሩኅሩኅና አንጸባራቂ ልብ ይኑ ርህ፡፡
የመንፈስ ልጅ ሆይ!
በእኔ ዘንድ ከሁሉም ይበልጥ ተወዳጅ ፍትሕ ናት፤ እኔን የምትሻ ከሆነ ፊትህን አታዙር ባት፣ ምሥጢሬንም አካፍልህ ዘንድ ቸል አትበ ላት፡፡ በእርሷ እርዳታ በሌሎች ሰዎች ዓይኖች ሳይሆን በዓይኖችህ ታያለህ፣ በጎረቤትህም ዕው ቀት ሳይሆን በራስህ ዕውቀት ታውቃለህና፡፡ እን ዴት መሆን እንደሚገባህ ይህን በልብህ አሰላ ስል፡፡ በእውነቱ ፍትሕ ለአንተ ስጦታዬና የፍ ቅራዊ ደግነቴ ምልክት ናት፡፡ እንግዲህ በዓይኖ ችህ ትይዩ አኑራት፡፡
የሰው ልጅ ሆይ!
ሊታወስ በማይቻል ሕያውነቴና፣ በጥንቱ ዘለዓ ለማዊ ህላዌዬ ተሸፍኜ፣ ለአንተ ያለኝን ፍቅር አወቅሁ፤ ስለዚህም ፈጠርኩህ አምሳሌንም ቀረ ጽኩብህ፣ ውበቴንም ገለጽኩልህ፡፡
የሰው ልጅ ሆይ!
ያንተን መፈጠር ወደድኩ፣ ስለዚህም ፈጠር ኩህ፡፡ እንግዲህ ስምህን እንዳነሳና ነፍስህን በሕ ይወት መንፈስ እሞላት ዘንድ አንተም አፍቅ ረኝ፡፡
የሕያው ልጅ ሆይ!
አፍቅረኝ አፈቅርህ ዘንድ፡፡ ባታፈቅረኝ ግን የእ ኔም ፍቅር በምንም ዓይነት ሊደርስህ አይች ልም፡፡ ይህንን እወቅ፣ አገልጋይ ሆይ፡፡
የሕያው ልጅ ሆይ!
ገነትህ ፍቅሬ ነው፤ መንግሥተ-ሰማያዊ ቤት ህም ከእኔ ጋር እንደገና መገናኘት ነው፡፡ ወደ ዚያ ግባ አትዘግይም፡፡ ይህ ያ በላይኛው መን ግሥታችንና በከፍተኛው ግዛታችን የተመደበ ልህ ነው፡፡
የሰው ልጅ ሆይ!
እኔን ካፈቀርከኝ ከራስህ ፊትህን አዙር፤ የእኔንም ፍላጎት ከፈለግህ የራስህን አትሻ፤ አንተ በእኔ ውስጥ እንድትሞትና እኔ በአንተ ውስጥ ለዘለ ዓለም እኖር ዘንድ፡፡
የመንፈስ ልጅ ሆይ!
ራስህን ክደህ ወደ እኔ በመመለስ በስተቀር ሰላም አይኖርህም፤ እኔ ለብቻዬ ከሁሉ በላይ መወደድን ስለምሻ፣ በራስህ ስም ሳይሆን በስሜ መመካት፣ እምነትህንም በራስህ ላይ ሳይሆን በእኔ ላይ መጣል ይገባሃል፡፡
የሕያው ልጅ ሆይ!
ፍቅሬ ምሽጌ ነው፤ ወደዚያ የሚገባ ደህንነትና ዋስትና አለው፤ ፊቱን ከዚያ የሚያዞር ግን በእ ርግጥ ተንከራትቶ ይጠፋል፡፡
የልሳን* ልጅ ሆይ!
አንተ ምሽጌ ነህ፤ ከውስጡም ግባ በሰላም ትኖር ዘንድ፡፡ ፍቅሬም በውስጥህ ነው፣ እወቀው፣ በቅርብህ ታገኘኝ ዘንድ፡፡
የሕያው ልጅ ሆይ!
አንተ ፋኖሴ ነህ ብርሃኔም በውስጥህ አለ፡፡ ከእ ሱም ብሩህነትን አግኝ፣ ከእኔም በስተቀር ሌላ አትሻ፡፡ ባለጸጋ አድርጌ ፈጥሬህ በረከቴንም በብ ዛት በላይህ አዝንቤአለሁና፡፡
የሕያው ልጅ ሆይ!
በሥልጣን እጅ ሠራሁህ፣ በብርቱም ጣቶች ፈጠ ርኩህ፤ በአንተም ውስጥ የብርሃኔን ህላዌ አኖ ርኩ፡፡ በዚያ እርካ፣ ሌላ ምንም አትሻ፤ ሥራዬ ፍጹም ትእዛዜም ጥብቅ ነውና፡፡ አትፈትነው፣ ጥርጣሬም አይግባህ፡፡
የመንፈስ ልጅ ሆይ!
ሀብታም አድርጌ ፈጠርኩህ፣ ለምን ራስህን ወደ ድህነት ታወርዳለህ? ክቡር አደረግኩህ፣ ለምን ራስህን ታዋርዳለህ? ከዕውቀት ህላዌ ሕያውነ ትን ሰጠሁህ፣ ለምን ከእኔ በስተቀር ከሌላ የዕ ውቀት ብርሃን ትሻለህ? ከፍቅር አፈር ሠራሁህ፣ እንዴት ራስህን ከሌላ ጋር ታወዳጃለህ? እይታ ህን ወደ ራስህ መለስ አድርግ፤ በውስጥህ ኃያል፣ ኃይል የተመላሁና በገዛ ራሱ ነዋሪ ሆኜ ቆሜ ታገኘኝ ዘንድ፡፡
የሰው ልጅ ሆይ!
አንተ ግዛቴ ነህ፣ ግዛቴም አይጠፋም፤ ለምን እጠፋለሁ ብለህ ትፈራለህ? ብርሃኔ ነህ ብርሃ ኔም ከቶ አይጠፋም፣ ለምን ስለመጥፋት ትሰጋ ለህ? ክብሬ ነህ ክብሬም አይቀንስም፤ ካባዬ ነህ ካባዬም ከቶ አያረጅም፡፡ ስለዚህ ለኔ ባለህ ፍቅር ጸንተህ ኑር፤ በክብር ግዛት ታገኘኝ ዘንድ፡፡
የልሳን ልጅ ሆይ!
ፊትህን ወደ ፊቴ መልስ፤ ከኔም በስተቀር ሁሉ ንም ተው፤ ልዕልናዬ ነዋሪ፣ ግዛቴም አይጠፋ ምና፡፡ ከኔ በስተቀር ሌላ ብትሻ፣ አዎን፣ እስከ ዘለዓለምም በፍጥረተ-ዓለም ውስጥ ብትፈል ግም እንኳ፣ ፍለጋህ ከንቱ ይሆናል፡፡
የብርሃን ልጅ ሆይ!
ከእኔ በስተቀር ሁሉንም ረስተህ፣ ከመንፈሴ ጋር ተቋረብ፡፡ የትእዛዜ ፍሬ ነገር ይህ ነው፣ ስለዚህ ወደ እዚያ ተመለስ፡፡
የሰው ልጅ ሆይ!
በኔ እርካ፤ ሌላም ረዳት አትሻ፡፡ ምንጊዜም ከእኔ በስተቀር ሌላ የሚያረካህ የለምና፡፡
የመንፈስ ልጅ ሆይ!
እኛ ለአንተ የማንመኘውን አትጠይቀኝ፣ ለአንተ ብለን በአዘዝነው እርካ፣ ራስህንም በዚህ ካረካህ፣ የሚጠቅምህ ይህ ነውና፡፡
የአስደናቂው ራዕይ ልጅ ሆይ!
አፍቃሪዬ እንድትሆን፣ በውስጥህ የራሴን መን ፈስ እስትንፋስ ተንፍሼአለሁ፡፡ ለምን እኔን ትተህ ሌላ ተወዳጅ ፈለግህ?
የመንፈስ ልጅ ሆይ! ካንተ የሚጠበቀው ብዙ ነው፤ ሊረሳ አይችልም፡፡
ላንተ የተሰጠ ጸጋዬ የተትረፈረፈ ነው፣ ሊሸ ፈን አይችልም፡፡ ፍቅሬ መኖሪያውን ባንተ ውስጥ አድርጓል፣ ሊደበቅ አይችልም፡፡ ብርሃኔ ላንተ ተከ ስቷል፣ ሊጋረድ አይችልም፡፡
የሰው ልጅ ሆይ!
አንጸባራቂ ክብር ባለው ዛፍ ላይ እጅግ በጣም ምርጥ ፍሬዎችን አንጠልጥዬልሃለሁ፣ ስለምን ከዚያ ፊትህን አዙረህ ጥራቱ በአነሰው ረካህ? ስለዚህ በላይኛው ግዛት ወደሚሻልህ ተመለስ፡፡
የመንፈስ ልጅ ሆይ!
ክቡር አድርጌ ፈጠርኩህ፣ አንተ ግን ራስህን አዋ ረድህ፡፡ እንግዲህ ለተፈጠርክለት ዓላማ ትበቃ ዘንድ ተነሣ፡፡
የእርሱ፣ ከሁሉ የበላይ የሆነው ልጅ ሆይ!
እኔ ወደ ዘለዓለማዊው እጠራሃለሁ፣ አንተ ግን የሚጠፋውን ትሻለህ፡፡ የእኛን ፍላጎት ትተህ የራስህን እንድትሻ ያደረገህ ምን ይሆን?
የሰው ልጅ ሆይ! ወሰንህን አትለፍ፣ የማይገባህንም አትፈልግ፡፡
የኃይልና የሥልጣን ጌታ በሆነው በእግዚአብሔር ፊት ራስህን ድፋ፡፡
የመንፈስ ልጅ ሆይ!
በድሃ ላይ አትታበይ፣ በመንገዱ የምመራው እኔ ነኝና፣ የአንተንም ክፉ ምግባር ተመልክቼ፣ ለዘለዓለም ግራ አጋባሃለሁ፡፡
የሕያው ልጅ ሆይ!
እንዴት የራስህን ጉድለት ዘንግተህ በሌሎች ጉድ ለት ላይ ታተኩራለህ? እንዲህ የሚያደርግ ሁሉ በእኔ ዘንድ የተረገመ ነው፡፡
የሰው ልጅ ሆይ!
አንተው ራስህ ኃጢአተኛ ስለሆንክ ስለሌሎች ኃጢአት አትተንፍስ፡፡ ይህን ትእዛዝ ከተላለ ፍክ፣ የተረገምክ ትሆናለህ፣ ለዚህም እኔ እመ ሰክራለሁ፡፡
የመንፈስ ልጅ ሆይ!
በእውነቱ ዕወቅ፡- ሰዎችን በፍትሕ እንዲሠሩ እየመከረ ራሱ ግን ኃጢአትን የሚሠራ፣ ምንም እንኳ በስሜ ቢጠራ፣ ከእኔ አይደለም!
የሕያው ልጅ ሆይ!
በራስህ ላይ የማታደርገውን በሌላው ላይ አታ ድርግ፤ የማትፈጽመውንም አትናገር፡፡ ይህ ለአ ንተ ትእዛዜ ነው፣ አክብረው፡፡
የሰው ልጅ ሆይ!
አገልጋዬ ምንም ነገር ከአንተ ቢጠይቅ አትን ፈገው፣ ገጹ ገጼ ነውና፤ ስለዚህ በፊቴ እፍረት ይሰማህ፡፡
የሕያው ልጅ ሆይ!
ለጥያቄ ከመጠራትህ በፊት ራስህን በየዕለቱ ተቆጣጠር፤ ሞት ሳያስጠነቅቅ ይመጣብህና፣ ስለ ምግባሮችህ ትጠየቃለህና፡፡
የእርሱ፣ ከሁሉ የበላይ የሆነው ልጅ ሆይ!
እኔ ሞትን የደስታ መልእክተኛ እንዲሆንልህ አድርጌአለሁ፡፡ ስለምን ታዝናለህ? ብርሃኑም ድምቀቱን እንዲያለብስህ አድርጌአለሁ፡፡ ለምን ራስህን ከዚያ ትጋርዳለህ፡፡
የመንፈስ ልጅ ሆይ!
በሚያስደስተው የብርሃን ዜና ሰላም እልሃለሁ፡- ተደሰት! ወደ ቅድስና መንበርም እጠራሃለሁ፤ ለዘለዓለም በሰላም ለመኖር እንድትችል፣ በዚያ ውስጥ ኑር፡፡
የመንፈስ ልጅ ሆይ!
የቅድስና መንፈስ እንደገና የመገናኘትን አስደሳች ዜና ያበስርሃል፤ ለምን ታዝናለህ? የኃይል መን ፈስ በእምነቱ ያጸናሃል፤ ለምን ራስህን ትጋር ዳለህ? የገጹ ብርሃን ይመራሃል፤ እንዴት መሳ ሳት ትችላለህ?
የሰው ልጅ ሆይ!
ከእኛ ከመራቅህ በቀር ኃዘን አይግባህ፡፡ ወደ እኛ በመመለስህና በመቅረብህም ካልሆነ በሌላ አት ደሰት፡፡
የሰው ልጅ ሆይ!
በልብህ ደስታ ሐሴትን አድርግ፣ ከእኔ ጋር ለመ ገናኘትና ውበቴን ለማንጸባረቅ ትበቃ ዘንድ፡፡
የሰው ልጅ ሆይ!
ውብ ካባዬን ከራስህ አትግፈፍ፣ ለዘለዓለም እን ዳትጠማ፣ ከድንቅ ምንጬ ድርሻህ እንዲያመል ጥህ አታድርግ፡፡
የሕያው ልጅ ሆይ!
ለእኔ ፍቅር ስትል በሕግጋቴ ተራመድ፤ የኔንም ፍላጎት የምትሻ ከሆነ አንተ ከምትፈልገው ተቆ ጠብ፡፡
የሰው ልጅ ሆይ!
ውበቴን የምታፈቅር ከሆነ ሕግጋቴን ቸል አት በል፣ የእኔንም መልካም ፈቃድ ለመቀዳጀት ከፈለግህ ምክሮቼን አትዘንጋ፡፡
የሰው ልጅ ሆይ!
ወሰን በሌለው ጠፈር ውስጥ ብትበርና የሰማይን ስፋት ብታቋርጥ እንኳ፣ ለትእዛዛችን ተገዥነት ንና በፊታችን ትሕትናን ካላሣየህ፣ ምንም ዕረ ፍት አታገኝም፡፡
የሰው ልጅ ሆይ!
የታላቅነቴን ምሥጢራት እገልጽልህና በዘለዓለ ማዊ ብርሃን በላይህ አበራ ዘንድ፣ እምነቴን አጉላ፡፡
የሰው ልጅ ሆይ!
በፀጋ እንድጎበኝህ፣ በፊቴ ራስህን ዝቅ አድርግ፡፡
ገና በምድር ላይ እያለህ ድልን እንድትጎናጸፍ፣ ለእምነቴ ድል ተነሳ፡፡
የሕያው ልጅ ሆይ!
በሰማዬ አስታውስህ ዘንድ በምድሬ ስሜን አስ ታውስ፣ የእኔ ዓይኖችና የአንተ የሚጽናኑት በዚህ መንገድ ነውና፡፡
የዙፋኑ ልጅ ሆይ!
መስሚያህ መስሚያዬ ነው፣ ስማበት፡፡ በእጅግ በጣም ውስጣዊ ነፍስህ ስለተከበረው ቅድስናዬ ለመመስከር እንድትችል፣ እኔም በውስጤ ስለ አንተ ታላቅ ደረጃ እንድመሰክር፣ ማያህ ማያዬ ነው፤ እይበት፡፡
የሕያው ልጅ ሆይ!
ከክብር መቅደስ በስተኋላ፣ በግርማ ጥላ ሥር ከእኔ ጋር ታርፍ ዘንድ፣ በእኔ መልካም ፈቃድ በመርካትና እኔ ለማዘው አመስጋኝ በመሆን፣ በመንገዴ የሰማዕትነት ሞትን እሻ፡፡
የሰው ልጅ ሆይ!
አሰላስል፣ አስተውል፡፡ ምኞትህ በአልጋ ላይ መሞት ነው? ወይስ በመንገዴ በሰማእትነት፣ ደምህን በአቧራ ላይ በማፍሰስ፣ የትዕዛዜ ክስተ ትና በላቀው ገነትም የብርሃኔ ገላጭ መሆን? አገልጋይ ሆይ፣ በትክክል አመዛዝን!
የሰው ልጅ ሆይ!
በውበቴ! በፊቴ ፀጉርህን በደምህ ማቅለም፣ ከሁ ለንተን-ዓለም መፈጠርና ከሁለቱ ዓለማት ብር ሃን ይበልጥ ታላቅ ነው፡፡ ስለዚህ አገልጋይ ሆይ፣ ለዚህ ለመብቃት ተጣጣር!
የሰው ልጅ ሆይ!
ለሁሉም ነገር ምልክት አለው፡፡ የፍቅር ምልክቱ በትእዛዜ ሥር ቻይነትና በፈተናዎቼ ጊዜም መታ ገስ ነው፡፡
የሰው ልጅ ሆይ!
ልክ አመጸኛ ይቅርታን፣ ኃጢአተኛም ምሕረ ትን እንደሚመኙ ሁሉ፣ እውነተኛ አፍቃሪም መከራን ይመኛል፡፡
የሰው ልጅ ሆይ!
በመንገዴ ሥቃይ ካልደረሰብህ፣ በእነዚያ በፈ ቃዴ በረኩት ሰዎች መንገዶች ለመራመድ እን ዴት ትችላለህ? ከእኔ ጋር ለመገናኘት በሚሰ ማህ ናፍቆትህ መከራዎች ካላሰቃዩህ፣ ለው በቴ ባለህ ፍቅር ብርሃን እንዴት ታገኛለህ?
የሰው ልጅ ሆይ!
መከራዬ ከእኔ አምላካዊ ጥበቃ ነው፣ ውጫዊው እሳትና በቀል ነው፤ ውስጣዊው ግን ብርሃንና ምሕረት ነው፡፡ ዘለዓለማዊ ብርሃንና የማይሞት መንፈስ ትሆን ዘንድ፣ በቶሎ ወደዚያ ገስግስ፡፡
ይህም ላንተ ትእዛዜ ነው፣ አክብረው፡፡
የሰው ልጅ ሆይ!
ሀብት ቢያጋጥምህ አትፈንጥዝ፣ ውርደትም ቢደርስብህ አትዘን፤ ሁለቱም ያልፋሉ፤ ከዚ ያም በኋላ አይኖሩም፡፡
የሕያው ልጅ ሆይ!
ድህነት ቢመጣብህ አትዘን፤ አንድ ቀን የሀብት ጌታ ይጎበኝሃልና፡፡ ውርደትንም አትፍራ፤ አንድ ቀን ክብር ትጎናጸፋለህና፡፡
የሕያው ልጅ ሆይ!
ልብህ በዚህ በዘለዓለማዊው፣ በማይጠፋው ግዛት፣ በዚህም ከጥንት በነበረው፣ ለዘለዓለ ምም በሚኖር ሕይወት ላይ የምያተኩር ከሆነ፣ ይህን ጠፊና በፍጥነት አላፊ ልዕልና ተው፡፡
የሕያው ልጅ ሆይ!
ወርቅን በእሳት እንፈትናለን፣ አገልጋዮቻችንንም በወርቅ እንፈትናለንና፣ ራስህን በዚህ ዓለም ነገር አታባክን፡፡
የሰው ልጅ ሆይ!
አንተ ወርቅን ትመኛለህ፣ እኔ ግን ከዚያ ነፃ እንድትሆን እፈልጋለሁ፡፡ አንተ ያንን በማግኘት ሀብታም የምትሆን ይመስልሃል፣ እኔ ግን ብል ጽግናህ ከዚያ የነፃህ ሲሆን መሆኑን አውቃለሁ፡፡
በሕይወቴ! ይህ ዕውቀቴ ነው፣ ያ ደግሞ ያንተ ከንቱ ምኞት ነው፤ የእኔ መንገድ ከአንተ [መን ገድ] ጋር እንዴት ሊስማማ ይችላል?
የሰው ልጅ ሆይ!
በሰማይ፣ ከማይደበዝዝ ድምቀት ማከማቻ ቤቶ ችና ክብራቸው ከማይጠፋው የሀብት ክምችት ትወስድ ዘንድ፣ ሀብቴን ለድሆቼ ለግስ፡፡ ነገር ግን በሕይወቴ! በእኔ ዓይን ለማየት ብትችል ኖሮ፣ ነፍስህን መስዋዕት ማድረጉ የበለጠ ክቡር ነገር ነው፡፡
የሰው ልጅ ሆይ!
የሰው አካል ዙፋኔ ነው፤ በዚያ እመሠረትና በዚያ እኖር ዘንድ ከሁሉም ነገሮች አንፃው፡፡
የሕያው ልጅ ሆይ!
ልብህ መኖሪያዬ ነው፤ ለማረፊያዬ ቀድሰው፡፡
መንፈስህ የመገለጫዬ ቦታ ነው፣ ለመከሰቻዬ አንፃው፡፡
የሰው ልጅ ሆይ!
እጅህን በጉያዬ ውስጥ አኑር፣ ብሩህና አንጸባ ራቂ ሆኜ በላይህ እሆን ዘንድ፡፡
የሰው ልጅ ሆይ!
እንደገና የመገናኘትን ሐሴት ታገኝ ዘንድ፣ ወደ ሰማዬ እረግ፤ ከማይጠፋው ክብር ጽዋም ተወዳ ዳሪ የሌለውን የወይን ጠጅ በብዛት ጠጣ፡፡
የሰው ልጅ ሆይ!
ከእውነት በራቁ እምነቶችህና በከንቱ አስተሳሰቦ ችህ ስትባዝን አያሌ ቀናት አለፉብህ፡፡ በአልጋህ ላይ የምታንቀላፋው እስከ መቼ ነው? ፀሐይ ወጥታ የመጨረሻ ከፍታዋ ላይ ደርሳለችና፣ ምናልባት በውበት ብርሃን ባንተ ላይ ታበራ ዘንድ፣ ራስህን ከእንቅልፍ ቀና አድርግ፡፡
የሰው ልጅ ሆይ!
ብርሃኑ ከተቀደሰው ተራራ አድማስ ባንተ ላይ በርቷል፤ የዕውቀት ብርሃን መንፈስም በልብህ ሲና ላይ ነፍሷል፡፡ ስለዚህ፣ ለዘለዓ ለማዊ ሕይወት ብቁ ሆነህ ከእኔ ጋር ለመገ ናኘት እንድትችል፣ ራስህን ከእውነት ከራቁ ከንቱ እምነቶች ግርዶሾች ነፃ አውጣና ወደ መንበሬ ግባ፡፡ ሞት፣ ድካምም ሆነ ችግር የማ ይመጣብህ በዚህ ሁኔታ ነው፡፡
የሰው ልጅ ሆይ!
ዘለዓለማዊነቴ የእኔ ፍጥረት ነው፣ ላንተ ፈጠ ሪኩት፡፡ የአካልህ መጎናጸፊያ አድርገው፡፡ አንድ ነቴ የእጄ ሥራ ነው፤ ላንተ ሠራሁት፤ እስከ ዘለዓለም ለዘለዓለማዊ ሕያውነቴ መገለጫ ትሆን ዘንድ፣ በዚያ ራስህን አጎናጽፍ፡፡
የሰው ልጅ ሆይ!
ግርማዬ ላንተ ስጦታዬ ነው፣ ታላቅነቴም ላንተ የምሕረቴ ምልክት ነው፡፡ ለኔ ተገቢ የሆነውን ማንም አይገነዘብም፣ እንዲሁም ማንም ሊገል ጸው አይችልም፡፡ በእውነቱ፣ ለአገልጋዮቼ ላለኝ የፍቅራዊ ደግነቴና ለሕዝቤ የምሕረቴ ምልክት እንዲሆን፣ በኅቡዕ ማከማቻ ቤቶቼና በትእዛዜ ግምጃ ቤቶች ውስጥ አኑሬዋለሁና፡፡
የመለኮታዊውና የስውሩ ህላዌ ልጆች ሆይ!
እኔን ከማፍቀር ትሰናከላላችሁ፣ ነፍሶችም እኔን ሲያነሱ ይጨነቃሉ፡፡ አዕምሮዎች ሊገነዘቡኝ ልቦ ችም ሊወስኑኝ አይችሉምና፡፡
የውበት ልጅ ሆይ!
በመንፈሴና በችሮታዬ! በምሕረቴና በውበቴ!
በሥልጣን አንደበት የገለጽኩልህ፣ በኃይል ብዕርም የጻፍኩልህ ሁሉ፣ በአንተ አቅምና የመ ረዳት ችሎታ መጠን እንጂ በሁኔታዬና በድ ምፄ ጣዕመ-ዜማ መጠን አይደለም፡፡
የሰዎች ልጆች ሆይ!
እኛ ሁላችሁንም ለምን ከአንድ ዓይነት አፈር እንደፈጠርናችሁ አታውቁምን? አንዱ ከሌላው ራሱን ከፍ እንዳያደርግ ነው፡፡ እንዴት እንደተ ፈጠራችሁ በልባችሁ ዘወትር አሰላስሉ፡፡ ሁላች ሁንም ከአንድ ዓይነት ነገር ስለፈጠርናችሁ፣ ከእ ጅግ በጣም ውስጣዊው ሕልውናችሁ በምግባራ ችሁና በሥራችሁ፣ የአንድነት ምልክቶችና የመ ላቀቅ ሕላዌ ይገለጽ ዘንድ፤ ልክ እንደ አንድ ነፍስ፣ በአንድ እግር የመራመድ፣ በአንድ አፍ የመብላትና በአንድ ምድር የመኖር ግዴታ አለ ባችሁ፡፡ የብርሃን ሠራዊት ሆይ! ለእናንተ ምክሬ ይህ ነው፡፡ አስደናቂ ክብር ካለው ዛፍ የቅድስና ፍሬ ታገኙ ዘንድ፣ ይህን ምክር ስሙ፡፡
እናንት የመንፈስ ልጆች ሆይ!
እናንተ ግምጃ ቤቴ ናችሁ፣ በእናንተ ውስጥ የም ሥጢሮቼን ሉሎችና የዕውቀቴን ዕንቁዎች አኑሬአቸዋለሁና፡፡ በአገልጋዮቼ መካከል ከሚ ገኙ ባዕዳንና በሕዝቦቼ መካከል ካሉት እም ነተ-ቢሶች ጠብቋቸው፡፡
የእርሱ፣ በእርሱነቱ መንግሥት በራሱ ሕልውና የቆመው ልጅ ሆይ!
እኔ የቅድስና መዓዛዎችን ሁሉ ላንተ ማርበቤን፣ ቃሌንም ሙሉ በሙሉ ላንተ መግለጼን፣ በአንተ አማካይነት በረከቶቼን ማሟላቴንና ራሴ የፈለግ ሁትንም ላንተ መሻቴን እወቅ፡፡ ስለዚህም በፈቃዴ እርካ፤ አመስግነኝም፡፡
የሰው ልጅ ሆይ!
እኛ የገለጽንልህን ሁሉ በብርሃን ቀለም በመንፈ ስህ ጽላት ላይ ጻፍ፡፡ ይህ ከአቅምህ በላይ ከሆነ፣ የልብህን ህላዌ ቀለምህ አድርገው፡፡ ይህንንም ለማድረግ ካልቻልክ፣ በመንገዴ በፈሰሰው በዚያ በደማቅ ቀይ ቀለም ጻፍ፡፡ ብርሃኑ ለዘለዓለም ይኖር ዘንድ፣ በእርግጥ ከሁሉ ይበልጥ የሚያስ ደስተኝ ይህ ነው፡፡
Persian Hidden Words BH00113
ለማወቅ አዕምሮ ለመስማትም ጆሮ ያላችሁ ሰዎች ሆይ!
የተወዳጁ የመጀመሪያ ጥሪ ይህ ነው፡- ምሥጢ ራዊው ሌሊት ዘማሪ ወፍ ሆይ! በመንፈስ የጽጌ ረዳ አትክልት ሥፍራ ውስጥ በቀር አትኑር፡፡
የፍቅር ሰለሞን መልእክተኛ ሆይ! የበጣም ተወዳጁን ሳባ ጥላ በስተቀር ሌላ መጠለያ አትሻ፣ ሞት-አልባ ወፍ* ሆይ! በታማኝነት ተራራ ላይ በስተቀር አትኑር፡፡ በነፍስህ ክንፎች ወሰን ወደ ሌለው ግዛት ብትመጥቅና ከግብህ ለመድረስ ብትሻ፣ መኖሪያህ በዚያ ነው፡፡
የመንፈስ ልጅ ሆይ!
ወፍ ጎጆዋን ትሻለች፤ ሌሊት ዘማሪ ወፍም የጽ ጌረዳን ውበት፤ እነዚያ የሰዎች ልቦች አእዋፍ ግን በአላፊው ትቢያ ረክተው፣ ከዘለዓለማዊ ጎጆ አቸው ርቀዋል፣ ዓይኖች ወደግዴለሽነት አዘቅት ስላተኮሩ፣ ከመለኮታዊ ቅርበት ክብር ተ ነፍገ ዋል ፡፡ አየ ጉድ! ምንኛ አስገራሚና አሳዛኝ ነው፤ ላንዲት ፍንጃል ሲሉ፣ ከሚያጥለቀልቁት የእ ጅግ በጣም ከፍተኛው ባሕሮች ፊታቸውን አዙ ረዋል፣ ከሁሉም በላይ አንጸባራቂ ከሆነው አድ ማስም ርቀው ይገኛሉ፡፡
ወዳጅ ሆይ!
በልብህ አትክልት ስፍራ ከፍቅር ጽጌረዳ በስተ ቀር ሌላ አትትከል፣ ከፍቅርና ከምኞት ሌሊት ዘማሪ ወፍዋም ላይ አያያዝህን አታላላ፡፡ ከጻድ ቃን ጋር መወዳጀትን አጥብቅ፤ ከእምነተ-ቢሶች ጋር ከመጎዳኘት ሁሉ ተጠበቅ፡፡
የፍትሕ ልጅ ሆይ!
አፍቃሪው ተፈቃሪው ወዳለበት አገር በቀር ወዴት ሊሄድ ይችላል? ማንስ ፈላጊ ነው፣ ከልቡ ምኞት በመራቅ እረፍት የሚያገኘው? ለእውነ ተኛ አፍቃሪ መገናኘት ሕይወት፣ መለያየት ግን ሞት ነው፡፡ ኅሊናው ትዕግሥት-አልባ ልቡም ሰላም የለውም፡፡ ወደ ፍቅረኛው መኖ ሪያ ለመገስገስ እልፍ አዕላፍ ሕይወትን ይተ ዋል፡፡
የትቢያ ልጅ ሆይ!
እውነት እልሃለሁ፡- ከሰዎች ሁሉ ይበልጥ ደንታ ቢስ በከንቱ የሚከራከርና ራሱን ከወንድሙ ለማስ በለጥ የሚሻው ነው፡፡ እንዲህ በሉ፣ ወንድሞች ሆይ! ማጌጫችሁ ተግባራት እንጂ ቃላት አይ ሁኑ፡፡
የአፈር ልጅ ሆይ!
በእውነቱ እወቅ፣ ከልቡ እጅግ በጣም አነስተኛዋ የቅናት ቅሪት እንኳ ገና ያልወጣች፣ ወደ ዘለዓለ ማዊው ግዛቴ ከቶ አይደርስም፣ ከንጽሕና መንግ ሥቴም የሚነፍሰውን የቅድስና ጣፋጭ መዓዛ አያሸትም፡፡
የፍቅር ልጅ ሆይ!
ክብር ከተመሉት ከፍታዎችና ከመንግሥተ-ሰማ ያዊ የፍቅር ዛፍ የምትርቀው በአንዲት እርምጃ ብቻ ነው፡፡ አንድ እርምጃ ውሰድና በሚቀጥለው ወደማይጠፋው ግዛት በመራመድ ወደ ዘለዓለማ ዊው አዳራሽ ግባ፡፡ ከዚያም በክብር ብዕር ለተገለ ጸው ጆሮህን አቅና፡፡
የክብር ልጅ ሆይ!
በቅድስና መንገድ ፍጠን፣ ከእኔ ጋር ወደ መቋ ረብ ሰማይም ግባ፡፡ ልብህን በመንፈስ መወልወያ አንጻ፣ የፍጹም ከፍተኛው ወደሆነው መንበርም በፍጥነት ገስግስ፡፡
በቅጽበት አላፊ ጥላ ሆይ!
ከመጠራጠር ዝቅተኛ ደረጃዎች አልፈህ ወደ እር ግጠኛነት የተከበሩ ከፍታዎች ውጣ፡፡ ያልተጋረ ደውን ውበት አይተህ በአድናቆት፡- ከፈጣሪዎች ሁሉ ፍጹም የላቀው ጌታ የተቀደሰ ይሁን! በማ ለት ትጮህ ዘንድ፣ የእውነትን ዓይን ግለጥ፡፡
የምኞት ልጅ ሆይ!
ለዚህ ጆሮህን አቅና፡- ሟች ዓይን ዘለዓለማዊ ውን ውበት ሊያውቅ ፍጹም አይችልም፣ በድን ልብም በጠወለገ አበባ እንጂ በሌላ አይደሰትም፡፡
መሰል መሰሉን ይሻል፣ ከመሰሉም ጋር ሲጎ ዳኝ ይደሰታልና፡፡
የትቢያ ልጅ ሆይ!
ውበቴን ማየት ትችል ዘንድ፣ ዓይኖችህን ጋርድ፤ የድምፄንም ጣፋጭ ጣዕመ-ዜማ ትሰማ ዘንድ፣ ጆሮዎችህን ድፈን፤ ከዕውቀቴም እንድትሳተፍ፣ ከዕውቀት ሁሉ ራስህን አንጻ፤ ከዘለዓለማዊው ብልጽግናዬ ውቅያኖስ ዘላቂ ድርሻ እንድታገኝ፣ ከሀብት ራስህን አንጻ፡፡
በጠራ እይታ፣ በንጹህ ልብና በንቁ ጆሮ ወደ ቅድስናዬ መንበር ለመግባት እንድትችል፣ ዓይ ኖችህን ጋርድ፣ ማለትም፣ ከውበቴ በስተቀር ከሌላው ሁሉ፤ ለቃሌ በስተቀር ጆሮዎችህን ለሁሉም ድፈን፤ ከእኔ ዕውቀት በስተቀር ከሌላ ዕውቀት ሁሉ ራስህን አንጻ፡፡
ባለሁለት ዕይታዎች ሰው ሆይ!
አንዱን ዓይን ጨፍነህ ሌላውን ግለጥ፡፡ አንዱን ለዓለምና በውስጧም ላሉት ሁሉ ጨፍን፣ ሌላ ውን ለተወዳጁ የተቀደሰ ውበት ግለጥ፡፡
ልጆቼ ሆይ!
ከሰማይዋ እርግብ ጣዕመ-ዜማ ተነፍጋችሁ፣ ወደ ኋላ ወደ ፍጹም ውድቀት ጥላ ሥር እንዳትሰ ምጡ፣ በጽጌረዳዋም ውበት ላይ ሳታተኩሩ፣ ወደ ውሃና አፈር እንዳትመለሱ እፈራለሁ፡፡
ወዳጆች ሆይ!
ዘላዓለማዊውን ውበት፣ መሞት ባለበት ውበት አትለውጡ፣ ፍቅራችሁንም በዚህ ጠፊ የትቢያ ዓለም ላይ አታኑሩ፡፡
የመንፈስ ልጅ ሆይ!
የቅድስና ሌሊት ዘማሪ ወፍ ውስጣዊ ምሥጢ ራትን የማትገልጥላችሁ ጊዜ ይመጣል፤ እናን ተም ሁላችሁ ከሰማያዊው ጣዕመ-ዜማና ከላይ ኛው ድምጽ ትነፈጋላችሁ፡፡
የቸልተኝነት ህላዌ ሆይ!
እልፍ አዕላፍ ምሥጢራዊ ልሳናት በአንድ ንግ ግር ግልጸትን ያገኛሉ፡፡ እልፍ አዕላፍ ስውር ምሥጢራትም በአንድ ጣዕመ-ዜማ ይገለጻሉ፤ ሆኖም ያሳዝናል! አድማጭ ጆሮም ሆነ ተገን ዛቢ ልብ የለም፡፡
ጓደኞች ሆይ!
በቦታ ወደማይወሰነው የሚያስገቡት በሮች በሰ ፊው ተከፍተው ይገኛሉ፣ የተወዳጁም መኖሪያ በአ ፍቃሪዎች ደም አጊጧል፣ ሆኖም ከጥቂቶች በስ ተቀር ሌሎች ሁሉ ከዚህች ከመንግሥተ-ሰማ ያዊ ከተማ ተነፍገዋል፣ ከእነዚህ ከጥቂቶቹም እንኳ እፍኝ ከማይሞሉት በስተቀር ማንም ንጹህ ልብና የተቀደሰ መንፈስ ኖሮት አልተገ ኘም፡፡
እናንት በገነተ-አርያም ነዋዎች ሆይ!
በቅድስና ዓለማት ውስጥ፣ በመንግሥተ-ሰማያ ዊው ገነት አጠገብ፣ የላይኛው ግዛት ባልደረቦ ችና የተከበረው ገነት የማይሞቱ ነዋሪዎች የሚ ከቧት አዲስ የአትክልት ሥፍራ መከሰቷን ለእ ርግጠኛነት ልጆች አውጁ፡፡ ስለዚህ፣ ወደዚያ ደረጃ ለመድረስ፣ የፍቅርን ምሥጢራት ከደማቅ አበባዋ* ለመግለጽ፣ መለኮታዊና የላቀ ጥበብ ንም ምሥጢር ከዘለዓለማዊ ፍሬዋ ለመቅሰም ተጣጣሩ፡፡ እነዚያ እዚያ ገብተው የሚኖሩት ዓይ ኖቻቸው የተጽናኑ ናቸው፡፡
ወዳጆቼ ሆይ!
በእነዚያ በተቀደሱና በተባረኩ አካባቢዎች፣ እጅግ በጣም በተከበረው ገነት ውስጥ በተተከለው የሕ ይወት ዛፍ ጥላ ሥር፣ ሁላችሁም ከፊቴ የተሰባ ሰባችሁባትን ያችን እውነተኛና አንጸባራቂ ጧት ዘነጋችኋትን? እነዚህን ከሁሉም በላይ ቅዱስ የሆኑ ሶስት ቃላት ስናገር፣ በአድናቆት አዳ መጣችሁ፡- ወዳጆች ሆይ! ፈቃዳችሁን ከፈቃዴ አታስቀድሙ፣ ያልተመኘሁላችሁንም ከቶ አት መኙ፣ በዓለማዊ ምኞቶችና ፍላጎቶች የረከሱት ንም በድን ልቦች ይዛችሁ አትቅረቡኝ፤ ነፍሳች ሁን ብታነጹ ኖሮ በዚህች በአሁንዋ ሰዓት ያችን ቦታና እነዚያን አካባቢዎች ባስታወሳችሁና የንግ ግሬ እውነተኛነት ለሁላችሁም ግልጽ በሆነ ነበር፡፡
በአምስተኛው የገነት ጽላት ውስጥ፣ ከሁሉም በላይ ቅዱስ ከሆ ኑት መስመሮች በስምንተኛው ላይ እርሱ እንዲህ ይላል፡-
እናንት በግድ-የለሽነት አልጋ ላይ እንደበድን የተጋደማችሁ ሆይ!
ብዙ ዘመናት አለፉ፤ ውድ ሕይወቶቻችሁም ወደ ማክተማቸው ናቸው፤ ሆኖም ከናንተ ዘንድ እስካ ሁን አንዲት የንፅህና እስትንፋስ እንኳ ወደ ቅ ድስና መንበራችን አልደረሰችም፡፡ ምንም እንኳ በኢአማኒነት ውቅያኖስ ውስጥ ተዘፍቃችሁ የም ትገኙ ብትሆኑም፣ በከናፍሮቻችሁ ግን በአንዱ የአምላክ እውነተኛ እምነት እንደምታምኑ ትናገ ራላችሁ፡፡ እርሱን እኔ የምጸየፈውን ወደዳችሁ፣ ከጠላቴም ተወዳጃችሁ፡፡ ይሁን እንጂ፣ ስለ ምድሬ እናንተን መሰልቸትና በውስጧም ያሉት ሁሉ ከእ ናንተ መሸሽ ደንታ ሳይኖራችሁ፣ በመመጻደቅና በእርካታ ትራመዳላችሁ፡፡ ዓይኖቻችሁን ብትገ ልጡ ኖሮ፣ በእርግጥ፣ ከዚህ ዓይነት ደስታ እልፍ የመረረ ኃዘንን፣ ከዚህም ዓይነት ሕይወት ሞትን ራሱን በመረጣችሁ ነበር፡፡
አንተ የትቢያ ተንቀሳቃሽ ቅርጽ ሆይ!
እኔ ከአንተ ጋር መቋረብ እሻለሁ፤ አንተ ግን እምነትህን በእኔ ላይ አልጣልክም፡፡ የአመጽህ ሰይፍ የተስፋህን ዛፍ ቆርጦታል፡፡ በሁሉ ጊዜ ያት እኔ በቅርብህ ነኝ፤አንተ ግን ሁሌም ከኔ እን ደራቅህ ነህ፡፡ የማይጠፋ ክብር መረጥኩልህ፣ አንተ ግን ለራስህ ወሰን የሌለውን ውርደት መረ ጥክ፡፡ ጊዜ ሳለ ተመለስ፤ ዕድልህም አያምልጥህ፡፡
የምኞት ልጅ ሆይ!
ሊቃውንትና ጠቢባን ለረዥም ዘመናት፣ የንዑ ዱን ቅርበት ለመቀዳጀት ጥረው ግረው አልቻ ሉም፤ ዕድሜ ልካቸውን እርሱን ሲፈልጉ ኖሩ፣ ሆኖም የገጽታውን ውበት አላዩም፡፡ አንተ ያለ አንዳች ጥረት ከግብህ ደርሰሃል፣ ያላንዳች ፍለ ጋም የፍለጋህን ዓላማ አግኝተሃል፡፡ ይሁን እንጂ በእኔነት ግርዶሽ በጣም ከመሸፈንህ የተነሣ፣ ዓይ ኖችህ የተወዳጁን ውበት አላዩም፣ እጆችህም የካባውን ጠርዝ አልነኩም፡፡ እናንት ዓይን ያላ ችሁ፣ ተመልከቱና ተደነቁ፡፡
በፍቅር ከተማ ነዋሪዎች ሆይ!
ጠፊው አውሎ ነፋስ ዘለዓለማዊውን ሻማ በመ ፈታተን ላይ ነው፣ የሰማያዊው ወጣት ውበትም በትቢያ ጨለማ ተጋርዷል፡፡ የፍቅር ነገሥታት አለቃ በግፈኞች ሰዎች በደል ደርሶበታል፤ የቅ ድስና እርግብም በጉጉቶች ጥፍሮች ውስጥ ታስ ሯል፡፡ በክብር አዳራሽ ውስጥ ነዋሪዎችና ሰማያ ዊው ሠራዊት ሲያዝኑና ሲያለቅሱ፣ እናንተ ግን በቸልነኝነት ዓለም ውስጥ ትዝናናላችሁ፣ ራሳች ሁንም እንደ እውነተኛ ወዳጆች ትቆጥራላችሁ፡፡
አስተሳሰቦቻችሁ ምንኛ ከንቱዎች ናቸው!
እናንት ሞኞች፣ ሆኖም የጠቢብ ስም የያዛችሁ ሆይ!
እናንት በውስጣዊአችሁ ተኩላዎች የሆናችሁ፣ መንጋዎቼን ለማጥፋት እያደባችሁ ለምንድን ነው እረኞችን የሚያስመስል ልብስ የለበሳችሁ? እና ንተ ልክ ጎህ ሳይቀድ እንደምትወጣዋና አንጸ ባራቂና ብሩህ መስላ ወደ ከተማዬ የሚጓዙ ትን ወደ ጥፋት ጎዳና እንደምትመራው ኮከብ ናችሁ፡፡
እናንት ትክክለኛ መሳዮች ግን ውስጠ እርኩሶች ሆይ!
እናንት እንደጠራ ሆኖም መራር፣ ላይ ላዩ ንጹህ ኩል የሚመስል፣ ነገር ግን በመለኮታዊው ፈታኝ ሲቀመስ አንድም ጠብታ ተቀባይነት እንደሌለው ውሀ ናችሁ፡፡ አዎን፣ የፀሐይ ጨረር በትቢያና በመስተዋት ላይ እኩል ያርፋል፣ ሆኖም በአን ጸባራቂነት እንደ ኮከብና እንደ ምድር የተለያዩ ናቸው፡- እንዲያውም ልዩነቱ ሊለካ አይችልም፡፡
የቃል ወዳጄ ሆይ!
አንዴ አሰላስል፡፡ ለመሆኑ ወዳጅና ጠላት በአ ንድ ልብ ውስጥ መኖር አለባቸው ሲባል ሰምተህ ታውቃለህን? ስለዚህ ወዳጅ ወደ ቤቱ እንዲገባ ባዕዱን አስወጣ፡፡
የትቢያ ልጅ ሆይ!
የውበቴና የክብሬ መኖሪያ ከአደረግሁት፣ ከሰው ልብ በስተቀር፣ በሰማይና በምድር ያለውን ሁሉ አዝዤልሃለሁ፤ ሆኖም አንተ ቤቴንና መኖሪያ ዬን ከኔ ይልቅ ለሌላ ሰጠህብኝ፤ የቅድስናዬም ክስተት መኖሪያ ቤቱን በፈለገ ቁጥር ባዕድ በዚያ አገኘ፣ ማረፊያም በማጣቱ የተወዳጁ ወደ ሆነው ቤተ-መቅደስ በፍጥነት ተመለሰ፡፡ ይሁን እንጂ ውርደትህን ስለማልሻ ምሥጢርህን ሸፈ ንኩ፡፡
የምኞት ህላዌ ሆይ!
ብዙ ማለዳዎች ቦታ ከማይወስናቸው ዓለማት ፊቴን ወደ አንተ መኖሪያ አዞርኩ፣ ከእኔም ጋር ሳይሆን ከሌሎች ጋር በድሎት አልጋ ላይ ስት ባዝን አገኘሁህ፡፡ ከዚያም በኋላ፣ እንደመንፈስ ቅጽበት ወደ መንግሥተ-ሰማያዊ ክብር ዓለማት ተመለስኩ፣ በላይኛውም መኖሪያዬ ለቅድስና ሠራዊቶች አልተነፈስኩም፡፡
የበረከት ልጅ ሆይ!
ምንም ከሌለ ባዶ ነገር በትእዛዜ አፈር እንድት ገኝ አደረግኩህ፣ እያንዳንዱን አቶምና የተፈጠ ሩትን ነገሮች ሁሉ ህላዌ ለአንተ መሰልጠኛ እን ዲሆኑ አዘዝኩ፡፡ እንዲሁም ከእናትህ ማሕፀን ከመውጣትህ በፊት የአንጸባራቂ ወተት ሁለት ምንጮች፣ የሚጠብቁህ ዓይኖችና የሚያፈቅሩህ ልቦችን አዘጋጀሁልህ፡፡ በምሕረቴ ጥላ ሥር ከፍ ቅራዊ ደግነቴ መገብኩህ፣ በጸጋዬና በችሮታዬ ህላዌም ጠበቅኩህ፡፡ የዚህ ሁሉ ዓላማዬ ከዘለዓ ለማዊ ግዛቴ ለመድረስ እንድትችልና ለማይታ ዩት ስጦታዎቼ ብቁ እንድትሆን ነበር፡፡ ይሁን እንጂ አንተ ደንታ-ቢስ ሆነህ ቀረህ፣ ሙሉ በሙሉ ከጎለመስክም በኋላ በረከቶቼን ሁሉ ዘነ ጋህ፤ ራስህን በከንቱ አስተሳሰቦችህ በጣም እንድ ትዋጥ ከማድረግህ የተነሣ፣ ጭራሽ ዝንጉ በመ ሆን፣ ከወዳጅ በራፍ ርቀህ፣ ከጠላቴ ግቢ እስከ መኖር ደረስክ፡፡
የዓለም ቁራኛ ባሪያ ሆይ!
ብዙ ማለዳዎች የፍቅራዊ ደግነቴ ልዝብ ነፋስ ባንተ ላይ ነፍሶ በግዴለሽነት አልጋ ላይ በከባድ እንቅልፍ ተውጠህ አገኘህ፡፡ ከዚያም ስለአሳዛኙ ሁኔታህ በዋይታ ወደ መጣበት ተመለሰ፡፡
የአፈር ልጅ ሆይ!
እኔን ማግኘት ከፈለግህ፣ ከኔ በስተቀር ሌላ አትሻ፤ ውበቴንም መመልከት ከፈለግህ፣ ዓይ ኖችህን ለዓለምና በውስጧም ላሉት ሁሉ ጨፍን፤ የእኔ ፈቃድና ከእኔ በስተቀር የሌላ ፈቃድ፣ ልክ እንደ እሳትና ውሃ፣ በአንድ ልብ አብረው ሊኖሩ አይችሉምና፡፡
የተወዳጀሁህ ባይተዋር ሆይ!
የልብህ ሻማ በኃይሌ እጅ በርቷል፣ በእኔነ ትና በኃይለኛ ስሜት ተፃራሪ ነፋሶች አታጥ ፋው፡፡ የሕመምህ ሁሉ ፈውስ እኔን ማስታ ወስ ነው፣ አትርሳው፡፡ ፍቅሬን ሀብትህ አድርገ ውና ልክ እንደ ዓይንህ ብርሃንና እንደ ሕይወ ትህ ተንከባከበው፡፡
ወንድሜ ሆይ!
የማር አንደበቴን አስደሳች ቃላት አድምጥ፣ ስኳር ከሚያፈሱ ከናፍሮቼ ከሚፈሰው ምሥጢ ራዊ የቅድስና ጅረት በብዛት ጠጣ፡፡ የዕውቀቴና የጥበቤ ልዩ መአዛ ያላቸው አበባዎች* በተቀደ ሰችው የልብህ ከተማ ለጋና ለምለም ሆነው ይበቅሉ ዘንድ፣ የመለኮታዊ ጥበቤን ዘሮች በን ጹህ የልብህ አፈር ላይ ዝራቸው፣ የእርግጠኝ ነት ውሀንም አጠጣቸው፡፡
የገነቴ ነዋሪዎች ሆይ!
በፍቅራዊ ደግነቴ እጆች የፍቅራችሁንና የወ ዳጅነታችሁን ታዳጊ ዛፍ በቅዱስ ገነት አትክ ልት ሥፍራ ውስጥ ተከልኩ፤ በመልካሙ የቸ ርነት ጸጋዬ ካፊያም አጠጣሁት፤ የማፍሪያው ጊዜ እሁን ስለደረሰ እንዲጠበቅ፣ በምኞትና በኃ ይለኛ ስሜት ነበልባልም እንዳይጋይ ለማድ ረግ ተጣጣሩ ፡፡
ወዳጆቼ ሆይ!
የስሕተትን ኩራዝ አጥፉ፣ በልቦቻችሁም ውስጥ የመለኮታዊ መርሖን ዘለዓለማዊ ችቦ አብሩ፡፡ በቅ ርቡ የሰው ልጆች መርማሪዎች፣ በሚሰገድለት ቅዱስ ዘንድ፣ ከንጹህ ባሕርይና እንከን ከሌለበት የቅድስና ተግባር በስተቀር ሌላ አይቀበሉምና፡፡
የትቢያ ልጅ ሆይ!
አሳላፊ፣ የያዘውን ጽዋ ፈላጊ እስኪያገኝ እንደ ማያቀርብና፣ አንድ ፍቅረኛም የተወዳጁን ውበት ሳያይ ከልቡ ጥልቀት እንደማያለቅስ ሁሉ፣ ሰሚ ካላገኙ የማይናገሩ ብልሆች ናቸው፡፡ ስለዚህ የመለኮታዊ ጥበብ ልዩ መዓዛ ያላቸው አበቦች ከማጥና ከአፈር ላይ ሳይሆን፣ ከልብ ላይ እስኪ ያብቡ ድረስ፣ የጥበብንና የእውቀትን ዘር በንጹህ የልብ አፈር ላይ ዝራቸውና ደብቃቸው፡፡
በመልእክቱ መጀመሪያ መስመር ላይ ይህ ተጽፎአል ተመዝ ግቧልም፣ በአምላክ ፅላት መቅደስም ውስጥም ተሸሽጓል፡-
አገልጋዬ ሆይ!
ለሚጠፋ ነገር ብለህ ዘለዓለማዊ ግዛትን አት ተው፤ ለዓለማዊ ምኞትም ብለህ መንግሥተ-ሰማ ያዊ ልዕልናን አትጣል፡፡ ይህ ከመሐሪው ብዕር ምንጭ የጎረፈው ዘለዓለማዊ የሕይወት ጅረት ነው፤ ከዚያም የሚጠጡ የበጃቸው ናቸው!
የመንፈስ ልጅ ሆይ!
ጎጆህን አፈራርሰህ እንደ ሞት-አልባዋ የፍቅር ወፍ ወደ ቅድስና ጠፈር ምጠቅ፡፡ ራስህንም በመ ካድ፣ በምሕረት መንፈስ ተሞልተህ በመንግ ሥተ-ሰማያዊ የቅድስና ግዛት ውስጥ ኑር፡፡
የትቢያ ልጅ ሆይ!
በአላፊ ቀን ድሎት አትርካ፣ ራስህንም ዘለዓለ ማዊ ዕረፍትን አትንፈግ፡፡ የዘለዓለማዊ ደስታ የአትክልት ሥፍራን በጠፊው ዓለም የትቢያ ቁልል አትለውጥ፡፡ ከእሥር ቤትህ በመውጣት ወደ ላይኛው የተከበሩ መስኮች ምጠቅ፣ ከፈ ራሽ ጎጆህም ወደ ቦታ-አልባ ገነት ብረር፡፡
አገልጋዬ ሆይ!
ራስህን ከዚህ ዓለም ሰንሰለት ነፃ አውጣ፣ ነፍስ ህንም ከእኔነት እሥር ቤት አላቅቅ፡፡ ዕድልህን አጥብቀህ ያዝ፣ ተመልሶ አይመጣልህምና!
የሴት አገልጋዬ ልጅ ሆይ!
የማይጠፋውን ልዕልና ብታይ ኖሮ፣ ከዚህ በቅጽ በት አላፊ ዓለም ለመራቅ በጣርክ ነበር፡፡
ነገር ግን አንዱን ከአንተ ሰውሮ ሌላውን መግ ለጽ ልበ-ንጹሐን ብቻ ሊረዱት የሚችሉት ምሥ ጢር ነው፡፡
አገልጋዬ ሆይ!
ልብህን ከክፋት አንፃና፣ ከቅናት ነፃ ሁነህ፣ ወደ ቅዱስነት መለኮታዊ መንበር ግባ፡፡
ወዳጆቼ ሆይ!
በወዳጁ መልካም ፈቃድ መንገድ ተራመዱ፣ የእ ርሱም ፍላጎት የፍጡሮቹ ፍላጎት መሆኑን ዕወቁ፡፡ ይህም ማለት፡- ማንም ሰው ያለ ወዳጁ ፈቃድ ወደ ወዳጁ ቤት መግባት፣ ወይም እጆ ቹን በሀብቱ ላይ ማሳረፍ፣ የራሱንም ፈቃድ ከባልንጀራው ፈቃድ ማስቀደም፣ በባልንጀራ ውም ላይ መጠቀምን በምንም ዓይነት መሻት የለበትም፡፡ እናንት ጠልቆ የመረዳት ችሎታ ያላ ችሁ፣ ይህን አሰላስሉ!
የዙፋኔ ጓደኛ ሆይ!
ክፉ ነገር አትስማ፣ መጥፎ ነገርንም አትይ፣ ራስህን አታዋርድ፣ እንዲሁም አትዘን፣ አታል ቅስ፡፡ ክፉ ነገር አትናገር፣ ባንተም ላይ ሲነገር እንዳትሰማ፣ የሌሎችን ስሕተት አታጉላ፣ የራ ስህ አይሎ እንዳይታይብህ፤ የማንንም ውርደት አትመኝ፣ የራስህ ወራዳነት እንዳይገለጽብህ፡፡
እንግዲህ በነፃነትና በእርካታ፣ ይህንን ሟች አካል ጥለህ፣ ወደ ረቂቋ ገነት ተመልሰህ በማ ይጠፋው መንግሥት ውስጥ ለዘለዓለም ትኖር ዘንድ፣ ከመቅጽበት ከሚያልፍ ጊዜ ያነሱትን የሕይወትህን ቀኖች፣ በአእምሮህ እንከን-አልባ፣ በልብህ ያልጎደፍህ፣ በሃሳብህ ንጹህ፣ በተፈጥ ሮህም የተቀደስክ ሆነህ ኑር፡፡
ወዮው! ወዮው! ዓለማዊ ምኞትን አፍቃሪዎች ሆይ!
ልክ እንደ መብረቅ በሆነ ፍጥነት በተወዳጁ አጠገብ አለፋችሁ፣ ልቦቻችሁንም ከእውነት በራቁ ሰይጣናዊ እምነቶች ላይ አሳረፋችሁ፡፡
በከንቱ አስተሳሰቦቻችሁ ፊት ተንበርክካችሁ እውነት ብላችሁ ትጠሩታላችሁ፡፡ ዓይኖቻች ሁን ወደ እሾህ አዙራችሁ፣ አበባ ብላችሁ ትሰ ይሙታላችሁ፡፡ አንድም ንጹህ ትንፋሽ አልተ ነፈሳችሁም፣ የመላቀቅ ልዝብ ነፋስም ከልቦቻ ችሁ መስኮች አልነፈሰም፡፡ የተወዳጁን ፍቅ ራዊ ምክሮች ወደ ነፋስ በትናችኋል፣ ከልቦቻ ችሁም ጽላት ፈጽሞ ደምስሳችኋቸዋል፣ ልክ እንደ ዱር አራዊትም፣ ህልውናችሁን በምኞትና በኃይለኛ ስሜት ግጦሽ ውስጥ በማኖር ትንቀ ሳቀሳላችሁ፡፡
በመንገዱ ወንድሞች ሆይ!
ተወዳጁን ማንሳቱን ቸል ያላችሁት፣ ከቅድስና ውም ቅርበት ርቃችሁ የቆያችሁት ለምንድን ነው? እናንት በከንቱ ውዝግብ እየባከናችሁ ሳላ ችሁ፣ የውበት ህላዌ ግን ወደር በሌለው አዳራሽ ውስጥ በክብሩ ዙፋን ላይ ተቀምጧል፡፡ የቅድስና ጣፋጭ መዓዛዎች በመተንፈስ ላይ ናቸው፣ የበረከትም ትንፋሽ ተናኝቷል፤ ሆኖም እናንተ ሁላችሁም በጠና ተሰቃይታችኋል፣ ከዚያም ተነፍጋችኋል፡፡ ለእናንተና ለእነዚያ የእናን ተን ፈለግ በመከተል በመንገዳችሁ ለሚራመዱት ወዮላችሁ!
የምኞት ልጆች ሆይ!
የከንቱ ውዳሴን ልብስ ጣሉ፣ የትዕቢትንም ልብስ አውልቁ፡፡
በማይታየው ብዕር በተጻፈውና በተመዘገበው ዕንቁ ጽላት ውስጥ ከሁሉም በላይ ቅዱስ ከሆኑት መስመሮች በሦስተ ኛው ላይ ይህ ተገልጿል፡-
ወንድሞች ሆይ!
እርስ በርሳችሁ ተቻቻሉ፣ ፍቅራችሁንም በዝቅ ተኛ ነገሮች ላይ አታድርጉ፡፡ በክብራችሁ አት ኩራሩ፣ መዋረድንም አትፍሩ፡፡ በውበቴ! ሁሉ ንም ነገሮች ከትቢያ ፈጠርኩ፣ እንደገናም ወደ ትቢያ እመልሳቸዋለሁ፡፡
የትቢያ ልጆች ሆይ!
ደንታቢስነት ወደ ጥፋት ጎዳና እንዳይመራቸው፣ የብልፅግናንም ዛፍ እንዳይነፍጋቸው፣ ለባለጸጎች ስለድሆች የመንፈቀ-ሌሊት ዋይታ ንገሩአቸው፡፡
መስጠትና መቸር የኔ ባሕርያት ናቸው፤ በባሕ ርያቴ ራሱን ያስጌጠ የበጀው ነው፡፡
የኃይለኛ ስሜት ህላዌ ሆይ!
ስግብግብነትን በሙሉ አስወግደህ እርካታን እሻ፤ ስግብግቡ ምንጊዜም ሲነፈግ፣ የሚረካው ግን ምን ጊዜም ይወደዳል፣ እንዲሁም ይመሰገና ልና፡፡
የሴት አገልጋዬ ልጅ ሆይ!
በድህነት ጊዜ አትጨነቅ፣ በሀብትም ላይ አት ተማመን፣ ድህነት በሀብታምነት ይተካል፣ ሀብ ታምነትም በድህነት ይተካልና፡፡ ሆኖም በአም ላክ በስተቀር በሌላው ሁሉ መደህየት ግሩም ስጦታ ነው፤ ዋጋውን አታቃልል፣ በመጨረሻው በአምላክ ባለፀጋ ያደርግሃልና፣ በዚህም መንገድ “በእውነቱ እናንተ ድሆች ናችሁ” የሚለውን አባባል ትርጉም ታውቃለህ፣ እንዲሁም “አምላክ ሁሉም ነገር ያለው ነው” የሚሉት ቅዱሳት ቃላት፣ ልክ እንደ እውነተኛ ንጋት፣ በአፍቃሪው ልብ አድ ማስ ላይ፣ ክብር በተመላበት ሁኔታ በአንጸባራ ቂነት ይነጋሉ፣ በሀብት ዙፋንም ላይ በአስተማ ማኝነት ይኖራሉ፡፡
የቸልተኝነትና የኃይለኛ ስሜት ልጆች ሆይ!
ከእኔ ይልቅ የሌላውን ፍቅር በልቦቻችሁ በማኖ ራችሁ፣ ጠላቴን ወደ ቤቴ እንዲገባ አደረጋችሁ፣ ወዳጄን ግን አስወጣችሁ፡፡ ለወዳጅ አነጋገር ጆሮ አችሁን አቅኑ፣ ወደ ገነቱም ፊታችሁን መልሱ፡፡
ዓለማዊ ወዳጆች፣ የራሳቸውን ጥቅም በመሻት፣ እርስ በርሳቸው የሚዋደዱ ይመስላሉ፣ እውነተ ኛው ወዳጅ ግን ለራሳችሁ ሲል ወዶአችኋል፣ ይወዳችኋልም፤ በእርግጥ እርሱ እናንተን ለመ ምራት ሲል ሥፍር ቁጥር የሌላቸውን ስቃዮች ተሰቃይቷል፡፡ እንዲህ ላለው ወዳጅ ታማኝነት ከማጉደል ይልቅ፣ ወደ እርሱ ተሽቀዳደሙ፡፡
ከስሞች ሁሉ ጌታ ብዕር አድማስ በላይ ጎህ የቀ ደደው፣ የእውነትና የታማኝነት ቃል የቀኑ ኮከብ እንዲህ ያለ ነው፡፡ በአደጋ ጊዜ ረዳቱ፣ በገዛ ራሱም ነዋሪው የሆነውን አምላክ ቃል ትሰሙ ዘንድ ጆሮአችሁን ክፈቱ፡፡
በጠፊ ሀብት ራሳችሁን የምታኩራሩ ሆይ!
ሀብት በተመራማሪውና በፍላጎቱ፣ በአፍቃሪውና በተወዳጁ መካከል ያለ ታላቅ መሰናክል መሆ ኑን በእውነት እወቁ፡፡ ባለጸጎች፣ ከጥቂቶቹ በስ ተቀር፣ እርሱ ወደሚገኝበት መንበር ለመድረስ ወይንም የእርካታና በጸጋ የመቀበል ከተማ ለመ ግባት በምንም ዓይነት አይችሉም፡፡ እንግዲህ፣ ባለጸጋ ሆኖ በብልጽግናው ከዘለዓለማዊ መንግ ሥት የማይታገድና በዚያም ከማይጠፋው ግዛት የማይነፈግ የበጀው ነው፡፡ ከሁሉም በላቀው ታላቁ ስም! ፀሐይ ለምድር ሕዝብ ብርሃን እን ደምትሰጥ ሁሉ፣ የእንዲህ ዓይነቱም ባለጸጋ ሰው አንጸባራቂነት ለሰማይ ነዋሪዎች ያበራል፡፡
በምድር ላይ ያላችሁ ባለጸጎች ሆይ!
በመካከላችሁ ያሉት ድሆች የእኔ አደራ ናቸው፤ አደራዬን ጠብቁ፣ በራሳችሁ የግል ድሎት ላይ ብቻ አታትኩሩ፡፡
የኃይለኛ ስሜት ልጅ ሆይ!
ከመላቀቅ ምንጭ የሞት-አልባ ሕይወትን ወይን ጠጅ በብዛት እንድትጠጣ ራስህን ከብልጽግና ርክሰት አንጻ፤ ወደ ድኅነት ዓለምም በፍጹም ሰላም ተሸጋገር፡፡
ልጄ ሆይ!
ከእኩያን ጋር መዋል ኀዘንን የሚያበዛ ሲሆን፣ ከጻድቃን ጋር መጎዳኘት ግን ዝገትን ከልብ ላይ ያነፃል፡፡ ከአምላክ ጋር መቋረብ የሚሻ፣ ራሱን ወደ እርሱ ተወዳጆች ወዳጅነት ያምራ፤ እንዲ ሁም የእምላክን ቃል ለመስማት የሚሻ ለእርሱ ኅሩያን ቃላት ጆሮውን ይስጥ፡፡
የትቢያ ልጅ ሆይ!
ተጠንቀቅ! ከእምነተ-ቢሱ ጋር አትሂድ፣ ከእር ሱም ጋር ወዳጅነትን አትሻ፤ እንዲህ ዓይነቱ ጓደኝነት የልብን ብርሃን ወደ ገሃነመ-እሳት ይለውጣልና፡፡
የሴት አገልጋዬ ልጅ ሆይ!
የመንፈስ ቅዱስን ጸጋ የምትሻ ከሆነ፣ ከጻድቅ ጋር ተወዳጅ፤ እርሱ ከማይሞተው አሳላፊ እጅ ከዘለዓለማዊ ሕይወት ጽዋ ስለጠጣ፣ ልክ እንደ እውነተኛው ንጋት፣ ለሙታን ልቦች ሕይወት ይሰጣልና፣ እንዲሁም ያበራቸዋልና፡፡
ግድየለሾች ሆይ!
የልብ ምሥጢሮች የተደበቁ አይምሰላችሁ፣ አይ ደሉም፣ በጉልህ ፊደላት ተቀርጸው በቅዱሱ ዘንድ በገሀድ የተገለጡ መሆናቸውን በእርግጥ ዕወቁ፡፡
ወዳጆች ሆይ!
በእውነት እላለሁ፣ በልቦቻችሁ የደበቃችሁት ማንኛውም ነገር ለእኛ እንደ ቀን ግልጽና የታወቀ ነው፤ የተደበቀውም በኛ ጸጋና ደግነት እንጂ፣ እናንተ የሚገባችሁ ሆናችሁ አይደለም፡፡
የሰው ልጅ ሆይ!
ጥልቀቱ ከማይለካው የምህረቴ ውቅያኖስ አንድ የጤዛ ጠብታ በዓለም ሕዝቦች ላይ አፈሰስኩ፣ ሆኖም እያንዳንዱ ከሰማያዊው የአንድነት ወይን ጠጅ ዙሮ ንጽህና ወደጎደለው የሚተነፈግ ዝቃጭ ስለተመለሰ፣ የማይጠፋውን ውበት ጽዋ አግልሎ በጠፊው ጽዋ ስለረካ፣ ፊቱን ወደ ዚያ የመለሰ አንድም አላገኘሁም፡፡ ያ የረካበ ትም አጸያፊ ነው፡፡
የትቢያ ልጅ ሆይ!
ከሞት-አልባው ተወዳጅ ወደር የሌለው ወይን ጠጅ ዓይኖችህን አታዙር፣ ለሚተነፍገውና ለሚ ጠፋው ዝቃጭም አትክፈታቸው፡፡ ጥበብ ሁሉ ያንተ እንዲሆን፣ ከማይታየው መንግሥት የሚ ጣራውንም ረቂቅ ድምፅ ለመስማት እንድትችል፣ ከመለኮታዊው አሳላፊ እጅ የሞት-አልባ ሕይወ ትን ጽዋ ተቀበል፡፡ እናንተ ዝቅተኛ ዓለማ ያላ ችሁ፣ ድምጻችሁን ከፍ አድረጋችሁ ጩሁ!
ቅዱሱንና የማይበላሸውን ወይን ጠጄን ትታችሁ ወደ ጠፊ ውሀ የተመለሳችሁት ለምንድነው?
እናንተ የዓለም ሕዝቦች ሆይ!
ያልተጠበቀ መከራ እየተከተላችሁ መሆኑን፣ ከባድ ቅጣትም እንደሚጠብቃችሁ በእርግጥ እወቁ፡፡ የፈጸማችሁት ድረጊት ከእይታዬ የተደ መሰሰ አይመስላችሁ፡፡ በውበቴ! ሥራዎቻችሁን ሁሉ ብዕሬ በጉልህ ፊደላት በአረንጓዴያማ ዕንቁ* ጽላቶች ላይ ቀረጾአቸዋል፡፡
በምድር ላይ ጨቋኞች ሆይ!
ለማንም ሰው ፍትህ አጉዳይነት ይቅርታ ላላደ ርግ ለራሴ ቃል ገብቻለሁና እጆቻችሁን ከጭቆና አንሱ ፡ ፡ ይህ በተጠበቀው ጽላት በማይሻር ሁኔታ የደነገግሁትና በክብር ማኅተሜ ያተምኩ በት ቃል ኪዳኔ ነው፡፡
ዐመጸኞች ሆይ!
ታጋሽነቴ ያደፋፈራችሁ፣ የረዥም ጊዜ በደል ቻይነቴም በጣም ግድየለሾች ያደረጋችሁ ከመ ሆኑ የተነሳ፣ ነበልባላዊውን የኃይለኛ ስሜት ፈረስ ቀስቅሳችሁ ወደ ጥፋት ወደሚያመሩት አደገኛ ጎዳናዎች ጋለባችሁ፡፡ ደንታቢስ አድር ጋችሁ አሰባችሁኝን ወይስ ያልተገነዘብኩ?
ስደተኞች ሆይ!
እኔን እንድታነሱበት የፈጠረኩትን አንደበት በዘ ለፋ አታርክሱት፡፡ የእኔነት እሳት ቢያሸንፋ ችሁ፣ እያንዳንዳችሁ ሌላውን ከማወቅ ይበልጥ ራሳችሁን በተሻለ ስለምታውቁ፣ የራሳችሁን ጉድለቶች እንጂ የፍጡራኔን ጉድለቶች አታስ ታውሱ፡፡
የምናብ ልጆች ሆይ!
አንጸባራቂው ንጋት ከዘላለማዊው ቅድስና አድ ማስ በላይ ጎህ በሚቀድበት ወቅት፣ ሰይጣናዊ ምሥጢሮችና በድቅድቅ ጨለማ የተሠሩት ድር ጊቶች፣ በዓለም ሕዝቦች ፊት እንደሚገለጡና እንደሚከሰቱ በእርግጥ እወቁ፡፡
ከትቢያ የምትበቅል አረም ሆይ!
ስለምን እነዚህ የቆሸሹ እጆችህ በመጀመርያ የራስህን ልብስ አልነኩም፣ ለምን በምኞትና በኃ ይለኛ ስሜት በረከሰው ልብህ ከኔ ጋር ለመቋረ ብና ወደተቀደሰው ግዛቴ ለመግባት ትሻለህ? ከምትመኘው ሩቅ፣ ሩቅ ነህ፡፡
የአዳም ልጆች ሆይ!
ቅዱሳት ቃላት፣ ንጹህና መልካም ሥራዎች ወደ መለኮታዊ ክብር ሰማይ ያርጋሉ፡፡ በቅርቡ፣ የሰው ልጆች መርማሪዎች በሚመለከው ቅዱስ ዘንድ፣ ከፍጹም መልካም ምግባርና በንጽኅናው እንከን ከሌለበት ተግባር በስተቀር ሌላ ስለማ ይቀበሉ፣ ምግባሮቻችሁ ከእኔነትና ከግብዝነት ትቢያ እንዲነጹና በክብር መንበር ተቀባይነትን እንዲያገኙ ለማድረግ ተጣጣሩ፡፡ ይህ ከመለኮ ታዊ ፈቃድ አድማስ በላይ የበራው የጥበብና የመለኮታዊ ምሥጢር የቀኑ ኮከብ ነው፡፡ ወደ እዚያም የሚመለሱ የተባረኩ ናቸው፡፡
የዓለማዊነት ልጅ ሆይ!
ለዚያ ከበቃህ የሕያው ዓለም አስደሳች ነው፣ መዋ ቲውን ዓለም ካለፍክ ዘላዓለማዊው ግዛት ክብር የተመላ ነው፤ ከመንግሥተ-ሰማያዊው ወጣት እጆች ከምሥጢራዊው ጽዋ ብትጠጣ የሚሰማህ ቅዱስ ሐሴት ጣፋጭ ነው፡፡ ለእዚህም ደረጃ ብትደርስ፣ ከመውደምና ከሞት፣ ከድካምና ከኃጢአት ነፃ ትሆናለህ፡፡
ወዳጆቼ ሆይ!
በተቀደሰው የዛማን አካባቢ በፓራን ተራራ ላይ ከእኔ ጋር የገባችሁትን ቃል-ኪዳን አስታውሱ፡፡
እኔ የላይኛውን ሠራዊትና በዘላለማዊው ከተማ ነዋሪዎችን ለምስክርነት ያዝኩ፣ ሆኖም አሁን ለቃል-ኪዳኑ ታማኝ የሆነ አንድም አላገኘሁም፡፡
በእርግጥ፣ ትእቢትና አመጽ አንዳችም ምልክት ሳያስቀሩ ከልቦች ላይ ደምስሰውታል፡፡ ሆኖም ይህንን እያወቅሁ ሳልገልጸው ጠበቅሁ፡፡
አገልጋዬ ሆይ!
አንተ ልክ በአፎቱ ጨለማ ውስጥ እንደተደበ ቀና ዋጋው ከጠቢቡ ዕውቀት እንደተሰወረ፣ በጥራት እንደተሠራ ሰይፍ ነህ፡፡ ስለዚህ ዋጋህ ለዓለም ሁሉ አንጸባራቂና ግልጽ ይደረግ ዘንድ፣ ከእኔነትና ከምኞት አፎት ውጣ፡፡
ወዳጄ ሆይ!
አንተ የቅድስናዬ ሰማያት የቀኑ ኮከብ ነህ፣ የዓ ለም እርኩሰት ድምቀትህን እንዲያደበዝዘው አታ ድርግ፡፡ ከደመናው በስተጀርባ አንጸባራቂ ሆነህ ወጥተህ፣ ሁሉንም ነገር በሕይወት ልብስ እን ድታለብስ፣ የደንታቢስነትን መጋረጃ ቅደድ፡፡
የትዕቢት ልጆች ሆይ!
በቅፅበት ለሚያልፈው ልዕልና ብላችሁ የማይ ጠፋውን ግዛቴን ተዋችሁ፣ እራሳችሁንም በተ ብለጭላጭ ዓለማዊ ልብሶች አስጊጣችሁ ይህን ንም መታበያ አደረጋችሁ፡፡ በውበቴ! ሁሉንም በባለ ቀለም የትቢያ ሽፋን ሥር ሰብስቤ፣ የእነ ዚያን የራሴን ከሚመርጡት በስተቀር፣ እነዚህን የተለያዪ ቀለማት ሁሉ እደመስሳለሁ፣ ይህም ከቀለማት ሁሉ ማንጻት ነው፡፡
የቸልተኝነት ልጆች ሆይ!
ፍቅራችሁን በሚያልፈው ልዕልና ላይ አድርጋ ችሁ በዚያ አትደሰቱ፡፡ እናንተ ልክ በቅርንጫፍ ላይ ሆና በልበ-ሙሉነት እንደምተዘምር፣ በድ ንገት አዳኙ ሞት መጥቶ በትቢያ ላይ እንደጣ ላት፣ ዝማሬዋ፣ ቅርጽዋና ቀለሟ ያለ ደብዛ እን ደጠፉት እንደ ዝንጉ ወፍ ናችሁ፡፡ ስለዚህም፣ የምኞት ባሮች ሆይ፣ ተጠንቀቁ!
የሴት አገልጋዬ ልጅ ሆይ!
መመሪያ ምንጊዜም በቃላት ይሰጥ ነበር፣ አሁን ግን በተግባር ተሰጥቷል፡፡ እያንዳንዱ ንጹህና ቅዱስ ተግባራት ማሳየት አለበት፣ ምክንያቱም ቃላት በተመሳሳይ ሁኔታ የሁሉም ንብረት ሲሆኑ፣ እነዚህን የመሳሰሉት ተግባራት ግን የተ ወዳጆቻችን ብቻ ናቸውና፡፡ ራሳችሁን በተግባራ ችሁ ለማሳወቅ፣ ከልብና ከነፍስ ጥረት አድርጉ፡፡
በዚህ ቅዱስና አንጸባራቂ መልእክት፣ በዚህ አኳኋን እንመክራችኋለን፡፡
የፍትሕ ልጅ ሆይ!
በጨለማ ወቅት የማይሞተው ሕያው ውበት ከታማኝነት ብሩህ አረንጓዴ* ከፍታ ወደ ሳድረ ቱል ሙንተሃ ተመልሶ በጣም መሪር ልቅሶ ስላ ለቀሰ የሰማያት ሠራዊትና የላይኛው ዓለማት ነዋሪዎች ስለኃዘኑ ዋይታ አሰሙ፡፡ ከዚያም ዋይታውና ልቅሶው ለምንድነው? ተብሎ ተጠየቀ፡፡
እርሱም መለሰ፡- እንደታዘዝኩት በታማኝነት ኮረብታ ላይ በተስፋ ተጠባበቅሁ፣ ሆኖም ከም ድር ነዋሪዎች የታማኝነት መዓዛ አላሸተትኩም፡፡
ከዚያም በኋላ እንድመለስ ስጠራ እነሆ! አንዳ ንድ የቅድስና ርግቦች በምድር ውሾች ጥፍ ሮች መሃል ክፉኛ ሲሰቃዩ ተመለከትኩ፡፡ ወዲ ያዉኑ የሰማይዋ አገልጋይ ፊቷን ተገልጣ እያ ንጸባረቀች ከሚሥጢራዊ አዳራሿ በፍጥነት በመ ውጣት ስማቸውን ጠየቀች፣ ከዚያም ከአንዱ በስተቀር የሁሉም ተነገረ፡፡ አጥብቆ ሲጠየቅ ከስሙ የመጀመሪያ ፊደል ተነገረ፣ በዚህም ጊዜ የሰ ማይ ክፍሎች ነዋሪዎች ከክብር መኖሪያቸው ፈጥነው ወጡ፡፡ ሁለተኛው ፊደል ሲነበብ አን ዳቸውም ሳይቀሩ ሁሉም በትቢያው ላይ ተደፉ፡፡
በዚያው ጊዜ ከእጅግ በጣም ውስጣዊ ቅዱስ ሥፍራ እንዲህ የሚል ድምጽ ተሰማ፡- “ይብቃ ከዚህ አይታለፍ”፡፡ በእውነቱ ላደረጉትና አሁንም በማድረግ ላይ ስላሉት እኛ እንመሰክራለን፡፡
የሴት አገልጋዬ ልጅ ሆይ!
ከማሐሪው አንደበት የመለኮታዊ ምሥጢርን ጅረት በብዛት ጠጣ፣ ከመለኮታዊ ልሳን የቀን ምንጭ የጥበብን የቀኑ ኮከብ ያልተጋረደ ውበት ተመል ከት፡፡ የመለኮታዊ ጥበቤን ዘሮች በንጹህ የልብ አፈር ላይ ዝራቸው፣ የእውቀትና የጥበብ የተ ለየ መዓዛ ያላቸው አበቦች ከተቀደሰው የልብ ከተማ ለጋና ለምለም ሆነው እንዲበቅሉ፣ የእር ግጠኝነትን ውሃዎች አጠጣቸው፡፡
የምኞት ልጅ ሆይ!
እስከመቼ በምኞት ዓለማት ውስጥ ታንዣብባ ለህ? ክንፎችን ያጎናጸፍኩህ፣ ወደ ምሥጢራዊ የቅድስና ዓለማት እንድትበር እንጂ፣ ወደ ሰይ ጣናዊ ምናብ አካባቢ እንድትበር አይደለም፡፡
ሚዶውን፣ ደግሞ፣ የሰጠሁህ፣ ሃር መሳይ ጉን ጉን ጸጉሬን እንድታበጥር እንጂ፣ አንገቴን እን ድትገዘግዝ አይደለም፡፡
አገልጋዮቼ ሆይ!
እናንተ የአትክልት ሥፍራዬ ዛፎች ናችሁ፤ እና ንተ እራሳችሁና ሌሎች ከዚያ ይጠቀሙ ዘንድ፣ መልካምና ግሩም ፍሬዎችን ማፍራት አለባ ችሁ፡፡ ስለዚህ በእደ-ጥበባትና በሙያ ዘርፎች መሰማራት የእያንዳንዱ ግዴታ ነው፣ የማስተ ዋል ሰዎች ሆይ! የብልጽግና ምሥጢር ያለው በእነዚህ ውስጥ ነውና፡፡ ውጤቶች የሚገኙት በየዘ ዴአቸው ነው፣ የአምላክም ጸጋ ፍጹም በቂ ይሆ ናችኋል፡፡ ፍሬ የማይሰጡ ዛፎች ለእሳት ናቸው፣ ለዘለአለምም እንዲሁ ይሆናሉ፡፡
አገልጋዬ ሆይ!
ከሰዎች መካከል እጅግ በጣም ወራዶች እነዚያ በምድር ላይ ፍሬ የማይሰጡት ናቸው፡፡ እንዲህ ያሉት ሰዎች በእውነቱ ከሙታን ጋር ይቆጠ ራሉ፣ እንዲያውም በአምላክ ፊት ከእነዚያ ከሥራ ፈቶችና ዋጋ-ቢስ ነፍሶች የሞቱት ይሻላሉ፡፡
አገልጋዬ ሆይ!
ከሰዎች ሁሉ ይበልጥ ምስጉኖች ለኑሮ የሚያ ስፈልገውን በሙያቸው የሚያገኙና የዓለማት ሁሉ ጌታ ለሆነው አምላክ ፍቅር ሲሉ ለራሳቸውና ለዘመዶቻቸው የሚያወጡት ናቸው፡፡
ምስጢራዊዋና አስገራሚዋ ሙሽራ፣ ከዚህ ቀደም በልሳን ሽፋን ሥር ተደብቃ፣ አሁን በአምላክ ጸጋና በመለኮታዊ ቸርነቱ፣ ልክ በተወዳጁ ውበት እንዳበራ አንጸባራቂ ብርሃን ተከስታለች፡፡
ወዳጆች ሆይ! ቸርነቱ ፍጹም፣ መከራከሪያው የተሟላ፣ ማረጋገጫው ግልጽ፣ ማስረጃውም የተረጋገጠ መሆኑን እመሰክራለሁ፡፡ ጥረታችሁ በመላቀቅ መንገድ ምን እንደሚገልጽ አሁን ይታይ፡፡ መለኮታዊው ቸርነት ለእናንተና ለእነ ዚያ በሰማይና በምድር ላሉት ተሟልቶ የተ ሰጠው በዚህ ሁኔታ ነው፡፡ የዓለማት ሁሉ ጌታ ለሆነው አምላክ ምስጋና ሁሉ ይሁን፡፡