Prayers & Meditations

Amharic · Bahá'u'lláh

Add range:

*በሃያ አራት ሰዓት ጊዜ ውስጥ አንዱ የሚደገረግ፣ ይህን ፀሎት ለመድገም የሚሻ ይቁምና ልቦናውን ወደ እግዚአብሔየር ያቅና፣ በሥፍራውም እንደቆመ የሩኅሩኁን የይቅር -ባዩን አምላክ ምሕረት እንደሚጠባበቅ ሁሉ ወደ ቀኝና ወደ ግራ ይመልከት፤ ከዚያም እንዲህ ይበል፤ *አቤቱ አንተ የስሞች ሁሉ ጌታና የሰማያት ፈጣሪ የሆንከው ሆይ! ፀሎቴ፣ ውበትህን እንዳላይ የጋረደኝን ግርዶሽ የሚያነድ እሳትና፣ ወደ ሕልውናህም ውቅያኖስ የሚመራኝ ብርሃን እንዲሆን፣ በእነዚያ ፣ ፍጹም የተከበረው የንዑዱና ሊታይ የማይቻለው አንተ ሕልውና ጎሕ በሆኑት እማፀንሃለሁ፤ *ቀጥሎም እግዚአብሔር የተባረከና የተከበረ ይሁንና፣ እጆቹን ወደ እርሱ በልመና በማንሳት እንዲህ ይበል፤ አቤቱ አንተ የዓለም እሾትና የብሔሮች ሁሉ ተወዳጅ የሆንከው ሆይ! ወደ አንተ ዞሬ፣ ከአንተ በቀር ከማንኛውም ቁራኛነት ሁሉ ተላቅቄ በእንቅስቃሴው መላው ፍጥረት በተቀሰቀሰበት ገመድህ ላይ ተንጠላጥዬ ታየኛለህ፡፡ ጌታዬ ሆይ እኔ አገልጋይህ የአገልጋይህም ልጅ ነኝ፡፡ ፈቃድንህና ፍላጎትህን ለመፈፀም ዝግጁ ሆኜ መቆሜንና ከበጎ ፈቃድህም በስቀር ሌላ እንደማልሻ ተመልከተኝ፤ አገልጋይህን እንደፈቀድከውና እንደሻህ እንድታደርገው በምሕረትህ ውቅያኖስና በጸጋህ የቀኑ ኮከብ (የዘመኑ ፀሐይ) እማጠንሃለሁ፡፡ ከመነገርና ከመወደስ በላይ በጣም ከፍ ባለው ኃያልነትህ! በአንተ የተገለፀ ማንኛውም ነገር የልቤ ፍላጎትና የነፍሴ ተወዳጅ ነው፤ እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ! ሰማያትንና ምድርን የከበበውን ፈቃድህን ተመልከት እንጂ ምኖቶቼንና አድራጎቶቼን አትመልከት፣ በፍጹም ታላቁ ስምህ አቤቱ አንተ የብሔሮች ሁሉ ጌታ ሆይ አንተ የፈለግኽውን ብቻ ፈልጌአለሁ፤ የምታፈቅረውንም ብቻ አፈቅራለሁ፡፡ ከዚያም በኋላ ተንበርክኮ ግንባሩን ወደ መሬት በመድፋት እንዲህ ይበል፡፡ ከራስህ ገለፃ በቀር ከማንም ገለፃ፣ ከአንተም የመረዳት ችሎታ በቀር ከማንም የመረዳት ችሎታ በላይ የላቅህ ነህ፡፡ *ቀጥሎም ይቁምና እንዲህ ይበል፤ *ጌታዬ ሆይ ፀሎቴን ሉዓላዊነትህ እስካለ ድረስ ለመኖርና በዓለማትህም እያንዳንዱ ዓለም ስምህን ላወሳበት የምችልበት፣ የህይወት ውሃዎች ምንጭ አደርግልኝ፤ *እንደገና በመማፀን እጆቹን ወደላይ በማንሳት እንዲህ ይበል፤ አቤቱ ከአንተ ሲለቀዩ ልቦችና ነፍሶች የቀለጡ በፍቅርህም እሳት መላው ዓለም የተቀጣጠለው ሆይ! አቤቱ አንተ በሰዎች ሁሉ ላይ ገዥ የሆንከው ሆይ! በአንተ ዘንድ የሚገኘውን እንዳትነፍገኝ፣ መላውን ፍጥረት ባንበረከክህበት ስምህ እማጠንሃለሁ፡፡ ጌታዬ ሆይ ይህ ባይተዋር በግርማህ ከለላ ሥር በምህረትህ ክልል ውስጥ ወዳለው፣ እጅግ በጣም ወደ ተከበረው ቤቱ ሲገሰግስ፣ ይህ ኃጢአተኛ የይቅር ባይነትህን ውቅያኖስ ይህ ዝቅተኛ የክብርህን መንበር፣ ይህ ምስኪን ፍጡር የሀብትህን ምንች ሲሻ ትመለከታለህ፤ የፈቀድከውን ማንኛውንም ነገር የማዘዝ ስልጣን ያንተ ነው፡፡ በሥራዎችህ መመስገን፣ ለትዕዛዞችህም ታዛዥነትን ማግኘት፣ ትዕዛዝ በመስጠጥም ገደብ የሌለብህ ሆነህ ፀንተህ የምትኖር መሆንህን እመሰክራለሁ፡፡ ቀጥሎም እጆቹን ወደላይ በማንሳት ከሁሉ በላይ ታላቁን ስም፣ ማለትም አላህ ኡ አብሃ (አምላ ፍጹም ክቡር) የሚለውን ሶስት ጊዜ ይደጋግም፡፡ አምላክ ይክበር ይመስገንና በእርሱ ፊት አንጎብሶ እጆቹን ጉልበቶቹ ላይ በማሳረፍ እንዲህ ይበል፤ አምላኬ ሆይ ፣ አንተን ለማምለክ በመናፈቁ አንተን ለማስታወስና ለማሞገስ በጣም በመመኘቱ መንፈሴ በመላው አካላቴ ውስጥ እንዴት እንደተንቀሳቀሰ ለዚያ በቃልህ መንግስትና በዕውቀትህ ሰማይ ትዕዛዝህ ልሳን ለመሠከረለትም መንፈሴ እንዴት እንደሚመሠክር ታያለህ፡፡ አቤቱ ጌታዬ በዚህ ሁኔታ የእኔን ምስኪንነት እንዳሳይና የአንተን በረከቶችና ፀጋዎች እንዳወሳ፣ የእኔን ደካማነት እንድመሠክርና የአንተን ሥልጣንና ኃያልነት እንድገልጽ፣ ከአንተ ጋር ያለውን ሁሉ ከአንተ መለመን እወዳለሁ፡፡ *ቀጥሎም ይቁም፣ በመማፀንም እጆቹን ሁለቱ ወደ ላይ ያንሳና እንዲህ ይበል፤ ከአንተ ከፍጹም ኃያሉ፣ ከፍጹም ለጋሱ በቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡ በመጀመሪያም ሆነ በመጨረሻ ሁሉን ደንጋጊ ከሆንከው፤ ከአንተ በቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡ በመጀመሪያም ሆነ በመቸረሻ ሁሉን ደንጋጊ ከሆንከው ከአንተ በቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡ እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ! ቅርታህ ድፍረትን ሰጥቶኛል፣ ምሕረትህ አጠንክሮኛል፣ ጥሪህ ቀስቅሶኛል ፀጋህም አስነስቶ ወደ አንተ መርቶኛል፡፡ እንግዲያውማ በቅርበትህ ከተማ በር ላይ ልቆም ከፈቃድህ ሰማይ ወደሚያበሩት ብርሃኖች ፊቴን ለመመለስ የምደፍር እኔ ማን ነኝ? ጌታዬ ሆይ፣ ይህ ጎስቋላ ፍጡር የፀጋህን በር ሲያንኳኳ ይህ ኢምንት ነፍስ ከበረከትህ እጆች ዘለዓለማዊውን የሕይወት ጅረት ሲሻ ትመለከታለህ፡፡ አቤቱ አንተ የስሞች ሁሉ ጌታ ሆይ፣ ትዕዛዝ ምንጊዜም ያንተው ነው፣ አቤቱ የሰማያት ፈጣሪ ሆይ የእኔ ግን ሁሉንም መተውና ለፈቃድህ በውዴታ መገዛት ነው፡፡ *ቀጥሎም እጆቹን ሶስቱ ወደ ላይ በማንሣት እንዲህ ይበል፤ እግዚአብሔር ከታላቅ ሁሉ ይበልጥ ታላቅ ነው፡፡ *ቀጥሎም ተምበርክኮ ግምባሩን ወደ መሬት በመድፋት እንዲህ ይበል፤ ወደ አንተ የቀረቡት የሚያቀርቡት ምስጋና ወደ ቅርበትህ ሰማይ ከመውጣት ወይም የእነዚያ ለአንተ ያደሩት ሰዎች ልቦች አፅዋፋት ወደ መንበርህ በር ከመድረስ በጣም ከፍ ያልክ ነህ፤ አንተ ከባህርያት ሁሉ የነፃህ ከስሞችም ሁሉ በላይ ቅዱስ መሆንህን እመሠክራለሁ:: ከአንተ ፍጹም ከላቀው ከንዑዱ በቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡ *ቀጥሎም ይቀመጥና እንዲህ ይበል፡- የተፈጠሩት ነገሮች ሁሉ ፣ የሰማይ ሰራዊት የገነት አርያም ነዋዎች ከእነዚህም በላይ ከፍጹም ደማቁ አድማስ የታላቁ አንደበት ራሱም የሚመሠክሩልህ፣ አንተ አምላክ መሆንህንና ከአንተም በስተቀር ሌላ አምላክ እንደሌለ ፣ እርሱም ያ የተከሰተው በእርሱም አማካይነት ሁ እና ን (ሁን) ፊደላት የተገናኙበትና የተጣመሩበት፣ ሥውሩ ምስጢር፣ ብርቁ ምልክት መሆኑን እመሰክራለሁ፡፡ ስሙ ከሁሉም በላይ ከፍተኛ በሆነው ብዕር የሠፈረው፣ በአምላክ መፃሕፍትም ውስጥ የተጠቀሰው፣ የሰማይና የምድር ዙፋን ጌታ እርሱ መሆኑን እመሰክራለሁ፡፡ *ቀጥሎም ቀጥ ብሎ ይቁምና እንዲህ ይበል፤ አቤቱ የፍጡራን ሁሉ ጌታና የሚታዩትም የማይታዩትም ነገሮች ሁሉ ባለቤት ሆይ! አንተ እምባዬንና የማሰማውን ሲቃ እነሆ ታስታውላለህ፤ የማቃሰቴን ድምፅ፣ ዋይታዬን የልቤንም ሰቆቃ ትሰማለህ፡፡ በኃያልነትህ ሕግ ተላላፊነቴ ወደ አንተ ከመቅረብ አግዶኛል፡፡ ኃጢአቴም ከቅድስናህ መንበር አግልሎኛል፤ አቤቱ ጌታዬ ፍቅርህ አበልጽጎኛል፤ ከአንተም መለየት አጥፍቶኛል፤ ከአንተ መራቅም ጨርሶኛል፡፡ በውበትህ ላይ ለማተኮርና በመጽሐፍህ ውስጥ ያሉትን ሁሉ ለማክበር እንድችል እንድትወስንልኝ በዚህ ምድረበዳ ባሉት ዱካዎችህ በዳር አልባ ስፋት ውስጥ እዚህ ነኝ፡፡ እዚህ ነኝ በሚሉት የሕሩያንህ ቃላት፣በግልፀትህ እስትንፋስናበክስተትህ የንጋት ልዝብ ነፋስ እማጠንሃለሁ፡፡ *ቀጥሎም ከሁሉም በላይ ታላቁን ስም ሶስት ጊዜ ይድገምና አጎንብሶ እጆቹን በጉልበቶቹ ላይ በማሳረፍ እንዲህ ይበል፤ አምላኬ ሆይ፣ አንተን እንዳስታውስና እንዳወድስህ ስለረዳኽኝ፣ እርሱን የምልክቶችህ ጎሕ የሆነውን ስላሳወቅኽኝ፣ በጌታነትህም ፊት እንድሰግድ ስለአደረግኽኝ፣ በአምላክነትህም ፊት ራሴን ዝቅ እንዳደርግና በታላቅነትህም አንደበት የተነገረውን ለመቀበል ስለአበቃኽኝ ምስጋና ለአንተ ይሁን፤ ከዚያም ይቁምና እንዲህ ይበል፤ እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ! ጀርባዬ በኃጢአቴ ክብደት ጎብጧል፣ ግዴለሽነቴም አውድሞኛል፡፡ የእኔን ርኩስ ድርጊቶችና የአንተን ደግነት ባሰላሰልኩ ቁጥር ልቤ በውስጤ ይቀልጣል፣ ደሜም በስሮቼ ውስጥ ይፈላል፡፡ በውበትህም አቤቱ አንተ የዓለም እሾት ሆይ! ፊቴን ወደ አንተ ለማቅናት እፍረት ይሰማኛል፣ ናፋቂ እጆቼም ወደ ቸርነትህ ሰማይ ለመዘርጋት ያፍራሉ፤ አቤቱ አንተ የሰማዩና የምድሩ ዙፋን ጌታ የሆንክ አምላክ ሆይ! እንባዎቼ አንተን ከማስታወስና የአንተንም ባህርያት ከማወደስ እንዴት እንዳገዱኝ እነሆ ታያለህ! አቤቱ አንተ የፍጡራን ሁሉ ጌታ፣ የሚታዩና የማይታዩ ነገሮች ሁሉ ንጉሥ የሆንከው ሆይ! ለተወዳጆችህ እንደልግስናህና እንደፀጋህ መጠን እንድታደርግላቸው በመንግስትህ ምልክቶችና በመግዛትህ ምሥጢራት እማጠንሃለሁ፡፡ ቀጥሎም ከሁሉም በላይ ታላቁን ስም ሶስቱ ይደገምና ተንበርክኮ ግንባሩን ወደ መሬት በመድፋት እንዲህ ይላል፡፡ አምላካችን ሆይ ወደ አንተ የሚያቀርበንንና በመፃሕፍትህና በቅዱሳት ጽሁፎችህ ውስጥ ያሉትን መልካም ነገሮች የሚያድለንን ስለላክህልን ምስጋና ለአንተ ይሁን፣ አቤቱ ጌታዬ ሆይ ከዋጋ ቢስ ሃሳብና ከከንቱ አስተሳሰብ አጀቦች እንድትጠብቀን እንማፀንሃለን፡፡ በእውነቱ አንተ ኃያሉ ሁሉን አዋቂው ነህና፡፡

  • ቀጥሎም ራሱን ቀና አድርጎ ይቀመጥና እንዲህ ይበል፤ አምላኬ ሆይ፣ ሕሩያንህ የመሠከሩትን እመሠክራለሁ፣ የገነት አርያም ነዋሪዎችም በኃያሉ ዙፋንህ ዙሪያ የከበቡት ሁሉ ያረጋገጡትንም አረጋግጣለሁ፡፡ አቤቱ የዓለማት ጌታ ሆይ የሰማይና የምድር መንግስታት የአንተ ናቸው፡፡ በየዕለቱ በሃያ አራት ሰዓት ጊዜ ውስጥ አንዴ 95 ጊዜ የሚደገም፤
በየዕለቱ ጧት እኩለ ቀንና ማታ የሚደረግ፣ ለመፀለይ የሚሻ ሁሉ እጁን ይታጠብ በመታጠብም ላይ ሳለ እንዲህ ይበል፡፡ አምላኬ ሆይ፤ መጽሐፍህን አጥብቆ እንዲይዝና የዓለምም አጀቦች በላዩ ላይ ኃይል እንዳይኖራቸው፣ እጄን አበርታ፡፡ የእርሱም ባልሆነው በማንኛውም ነገር ውስጥ እንዳይገባ ጠብቀው፡፡ በእውነቱ አንተ ፍጹም ኃያሉ፣ ከሁሉም በላይ ኃይል የተመላው ነህና፡፡ ቀጥሎ ፊቱን በመታጠብ ላይ እያለ እንዲህ ይበል፡፡ ጌታዬ ሆይ ፊቴን ወደ አንተ መልሻለሁ! በገጽህ ብርሃን አብራው፡፡ ወደ አንተም በቀር ወደ ማንም እንዳይዞር ጠብቀው፡፡
*ከዚያም ይቁም፣ ፊቱን ወደ ቂብሊሀ የውዳሴ ማዕከል ማለትም ወደ ባህጂ አቶር በመመለስ እንዲህ ይበል፤ ከእግዚአብሔር በስተቀር ሌላ አምላክ እንደሌለ ራሱ ይመሰክራል፡፡ የግልጽነትና የፍጥረት መንግስታት የእርሱ ናቸው፡፡ እርሱ በእውነቱ የግልፀት ጎህ የሆነውን በሲና ላይ የተነጋገረውን በእርሱም አማካይነት የላቀው አድማስ እንዲያበራ የተደረገውን፣ በእርሱም ሊታለፍ የማይቻለው የለውጥ ዛፍ የተናገረውን በእርሱም አማኝነት በሰማይና በምድር ላሉት ሁሉ፣ እነሆ የሁሉ ባለቤት የሆነው መጥቷል፡፡ ምድርና ሰማይ፣ ክብርና ግዛት የሰዎች ሁሉ ጌታ የላይኛውና የምድር ዙፋን ባለቤት የሆነው የአምላክ ናቸው፡፡ የሚለው ጥሪ የታወጀበትን ከስቶታል፡፡ *ከዚያም ያጎንብስና እጆቹን በጉልበቶቹ ላይ በማሳረፍ እንዲህ ይበል፤ አንተ ከእኔ ሙገሣና ከማንም ሰው ሙገሣ በላይ ከእኔ ገለፃና በሰማይና በምድር ካሉት ሁሉ ገለፃ በላይ የተከበርክ ነህ፡፡ *ከዚያም ቆሞ እጆቹን በመዘርጋት መዳፎቹንም ወደላይና ወደፊት በማቅናት እንዲህ ይበል፤ አምላኬ ሆይ፣ እርሱን በተማፃኘ ጣቶቹ በምሕረትህና በፀጋህ ዘርፍ ላይ የተንጠላጠለውን ቅር አታሰኘው፣ አቤቱ አንተ ምሕረትን ከሚያሳዩ ሁሉ ፍጹም መሐሪው ነህና! *ከዚያም ይቀመጥና እንዲህ ይበል፤ አንድነትህህና አንድዬነትህን አንተ አምላክ መሆንህን፣ ከአንተም በስተቀር ሌላ አምላክ እንደሌለ እመሰክራለሁ፤ በእውነቱ አንተ እምነትህን ገልፀሃል፣ ቃል-ኪዳንህንም አሟልተሃል፣ በሰማይ ውስጥና በምድር ላይ ለሚኖሩትም ሁሉ የፀጋህን በር በሰፊው ከፍተሃል፤ የዓለም ለውጦችና አጋጣሚዎች ወደ አንተ ከመመለስ ሊያደናቅፋአቸው ያልቻሉ፣ እና በአንተ ዘንድ ያለውን ለማግኘት ተስፋ በማድረግ ያላቸውን ሁሉ በሰውት በተወዳጆችህ ላይ ቡራኬና ሰላም፣ ሰላምታና ክብር ይረፍ፤ በእውነቱ አንተ ምንጊዜም ይቅር-ባዩ ፍጹም ፀጋ የተመላው ነህና፤
  • Naw-Ruz

ናውሩዝ መጋቢት 12 ቀን የባሃኢ ዓመት የመጀመሪያ ቀን እንዲሁም የደስታና የመስተንግዶ ዕለት ነው፡፡
አምላኬ ሆይ ለአንተ ፍቅር ሲሉ አንተን ከሚያስከፉ ነገሮች ሁሉ ተጠብቀው ለጾሙት የናውሩዝን ክብረ በዓል ስለሰየምክላቸው ምስጋና ለአንተ ይሁን፡፡ ጌታዬ ሆይ የአንተ ፍቅር እሳትና አንተ ባዘዝከው ፆም የተፈጠረው ግለት በእምነትህ እንዲነዱ፣ አንተንም በማመስገንና በማስታወስ የተወሰኑ እንዲሆኑ እንዲያደርጋቸው ፈቃድህ ይሁን፤ ጌታዬ ሆይ፣ አንተ ባዘዝከው ፆም ጌጥ እንዳስጌጥካቸው ሁሉ በፀጋህና ልግስና በተመላበት ደግነትህ የተቀባይነትህንም ጌጥ አጎናጽፋቸው፤ የሰዎች ሥራ ሁሉ ዋጋ የሚኖረው በአንተ መልካም ፈቃድ ሲደገፍ፤ በትዕዛዝህም ላይ ሲመሠረት ነውና አንተ ፆሙን ያላከበረውን እንደፆመ ብትቆጥረው አንዲህ ያለው ሰው ከእነዚያ ከእምቅድመ ዓለም ጀምረው ፆሙን ከአከበሩት ጋር ይቆጠራል፡፡ ፆሙን ያከበረውን እንዳልጾመ ብትመለከተው ያ ሰው የግልፀትህን ካባ በአቧራ እንዲቆሽሽ ከአደረጉትና ከዚህ ህያው ምንጭ የጠራ ውሃ እንዲወገዱ ከተደረጉት ጋር ይቆጠራል፡፡
አንተ፣ በእርሱ ፣ በስራዎቸህ ሁሉ ምስጉን ነህ የሚለው ዓርማ ከፍ የተደረገው ፤ ትዕዛዝህ ሁሉ የሚከበር ነህ ፤ የሚለውም ሰንደቅ በእርሱ አማካይነት የተዘረጋው ነህ፤ የሁሉም ነገር ልቀት በትዕዛዝህና በቃልህ ላይ ሲመሠረት ብቻ መሆኑን የእያንዳንዱም ተግባር ዋጋ በአንተ ፈቃድና በፍላጎትህ መልካም ፈቃድ እንደሚወሰን እንዲገነዘቡ፣ የሰዎችም ስራዎች ሁሉ ልጓም በአንተ ፈቃድና በትዕዛዝህ መዳፍ ውስጥ መሆኑን እንዲያውቁ፣ ይህን ደረጃህን ለአገልጋዮችህ ግለጽላቸው፣ ክርስቶስ አንተ የመንፈሱ (የየሡስ) አባት ሆይ፣ ስልጣን ሁሉ ያንተ ነው፤ በማለት በሚያወድስባቸው ፤ ወዳጅህም (መሐመድ) አንተ ከሁሉም በላይ ተወዳጅ የሆንከው ሆይ፣ ውበትህን ስለገለጽህ ከእነዚያ ከአንተ በቀር ከሌላው ሁሉ ከተላቀቁት ራሳቸውንም ወደ እርሱ አንተን ራስህን ገላጭና የባህርያትህ ክስተት ወደሆነው ካዞሩት በስተቀር ሌሎች ሰዎች ሁሉ እንዲያዝኑ ወደ ተደረጉበትወደ ታላቁ ስምህ ግልፀት ዙፋን ለመድረስ የሚያስችላቸውን ለተወዳጆችህ ስለፃፍክላቸው ክብር ላንተ ይሁን. በማለት በሚጮህባቸው በእነዚህ ቀናት ምንም ነገር ከውበትህ እንዳይጋርዳቸው ይህን እንዲያውቁ አድርጋቸው፤ ጌታዬ ሆይ፣ እርሱ የአንተ ቅርንጫፍ የሆነውና አጃቢዎችህ በሙሉ አንተን ለማስደሰት ባላቸው ጉጉት በመንበርህ ክልል ውስጥ ሆነው ፆማቸውን ከፆሙ በኋላ ዛሬ ፈስከዋል፡፡ ለእርሱም ለእነርሱም በእነዚያ ቀናት ወደ ቅርበትህ መድረክ ለገቡትም ሁሉ በመጽሐፍህ ውስጥ የወሰንከውን መልካም ነገር ሁሉ እዘዝ እዘዝላቸው፤ እንግዲህ በዚህም ህይወት በወዲያኛውም ህይወት የሚጠቅማቸውን አድላቸው፡፡ አንተ በእውነቱ ሁሉን አዋቂው ፍጹም ጠቢቡ ነህና፡፡

  • Fasting

ምስጋና ላንተ ይሁን፣ ጌታ አምላኬ ሆይ! ለእኔና አብረውኝ ላሉት ሁሉ፣ ከሁሉ በላይ ወደሆነው ክብርህ ሰማየ ሰማያት ለመምጠቅ የሚያስችለንንና ተጠራጣሪዎችን ወደ አንድነትህ መቅደስ ከመግባት ካገዱአቸው የጥርጣሬ ጉድፎች የሚያነፃንን እንድትልክልን፣ ጨለማውን ወደ ብርሃን በተለወጠበት፣ የሚዘወተረው መቅደስ በተገነባበት፣ ጽሁፍ መልእክት በተገለፀበትና የተዘረጋው ብራና ሽፋኑ በተነሳበት በዚህ ግልፀት እማጠንሃለሁ፡፡ ጌታዬ ሆይ እኔ ያ የአፍቃሪ ደግነትህን ገመድ አጥብቄ የያዝኩ፣ በምሕረትህና በለጋስነትህ ጠርዝ ላይ የተንጠላጠልኩ ነኝ፡፡ ለእኔና ለተወዳጆቼ የዚህኛውንና የመጪውን ዓለም መልካም ነገሮች ሁሉ አዘዝልን፤ እንግዲህ ከፍጡሮችህ መካከል እጅግ በጣም ምርጥ ለሆኑት ካዘዝክላቸው ሕቡዕ ሥጦታዎች አድላቸው፤ ጌታዬ ሆይ ፣ እነዚህ ቀናት አገልጋችህ ፆም እንዲፆሙባቸው ያዘዝካቸው ናቸው፡፡ ከአንተ በስተቀር ከሌሎች ነገሮች ሁሉ ራሱን አግልሎ ለአንተ ብቻ ሲል የፆመ የተባረከ ነው፡፡ ጌታዬ ሆይ አንተን እንድንታዘዝና ሕግጋትህን እንድናከብር እርዳኝ፣ እነርሱንም እርዳቸው፣ አንተ በእውነቱ የመረጥከውን ለማድረግ ኃይል አለህና፡፡ ከአንተ ከሁሉን አዋቂው፣ ከፍጹም ጠቢቡ በቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡ የዓለማት ሁሉ ጌታ ለሆነው የእግዚአብሔር ምስጋና ሁሉ ይሁን፤ በፆም ጊዜ የማለዳ አምላኬ ሆይ፣ ከቅርበትህ ከተማ በር አርቀህ እንዳትጥለኝና በፍጡሮችህ መካከል በፀጋህ ክስተቶች ላይ ያደረግሁአቸውን ተስፋዎች እንዳትቀጭብኝ፤ በኃያሉ ምልትህና በሰዎች መካከል በፀጋህ መገለጽ እማጠንሃለሁ፤ አምላኬ ሆይ፣ ፍጹም ቅዱሱን ፍጹም አንፀባራቂውን ፍጹም ኃያሉን ፍጹም ታላቁን ፍጹም የተከበረውንና ፍጹም ክብር የተመላውን ስምህን እንደያዝኩ፣ በዚህ ዓለምና በወዲያኛው ዓለም ያሉት ሁሉ በተንጠላጠሉበት የካባህ ዘርፍ ላይ ጠንጠላጥዬ ታየኛለህ፡፡ አምላኬ ሆይ፣ ሁልጊዜ ይበልጥ ወደ በርህ ደጀሰላም እንድታቀርበኝ፣ ከምህረትህ ጥላና ከቸርነትህ አጎበር እንድርቅ እንዳታደርገኝ በፍጹም ጣፋጩ ደምጽህና ፍጹም በተከበረው ቃልህ እማጠንሃለሁ፡፡ አምላኬ ሆይ፤ ፍጹም ቅዱሱን ፍጹም አንፀባራቂውን ፍጹም ኃያሉን ፍጹም ታላቁን ፍጹም የተከበረውንና ፍጹም ክብር የተመላውን ስምህን እንደያዝኩ፣ በዚህ ዓለምና በወዲያኛው ዓለም ያሉት ሁሉ በተንጠላጠሉበት የካባህ ዘርፍ ላይ ተንጠላጥዬ ታየኛለህ፡፡ አምላኬ ሆይ፣ በመጎናፀፊያህ መዓዛ እንድትስበኝና የቃልህን ምርጥ የወይን ጠጅ እንድጠጣ እንድታደርገኝ፣ በአንፀባራቂው የግምባርህ ውበትና ከፍጹም ከፍተኛው አድማስ በሚያበራው የገጽህ ብርሃን ብሩህነት እማጠንሃለሁ፡፡ አምላኬ ሆይ ፣ ፍጹም ቅዱሱን ፍጹም አንፀባራቂውን ፍጹም ኃያሉን ፍጹም ታላቁን ፍጹም የተከበረውንና ፍጹም ክብር የተመላውን ስምህን እንደያዝኩ፣ በዚህ ዓለምና በወዲያኛው ዓለም ያሉት ሁሉ በተንጠላጠሉበት የካባህ ዘርፍ ላይ ተንጠላትዬ ታየኛለህ፡፡
አምላኬ ሆይ ወደ ኋላ ሳላፈገፍግ ወይም እነዚያ በምልክቶችህ ያፌዙትና ከፊትህም የዞሩት በሚያቀርቡአቸው ሃሳቦች ሳልደናቀፍ እምነትህን እንዲገለግል በጣም እንድታነሳሳኝ፣ ልክ ፍጹም የተከበረው ብዕርህ በፍጥረትህ መንግስት ላይ የስውር ትርጉሞች ልዩ መዓዛ እያፈሰሰ በጽላቶችህ ገጾች ላይ እንደሚንቀሳቀስ ሁሉ በፊትህ ላይ በሚንቀሳቀሰው ፀጉርህ እማጠንሃለሁ፡፡ አምላኬ ሆይ፣ ፍጹመ ቅዱሱን ፍፁም አንፀባራቂውን ፍጹም ኃያሉን ፍጹም ታላቁን ፍጹም የተከበረውንና ፍጹም ክብር የተመላውን ስምህን እንደያዝኩ፣ በዚህ ዓለምና በወዲያኛው ዓለም ያሉት ሁሉ በተንጠላጠሉበት የካባህ ዘርፍ ላይ ተንጠላጥዬ ታየኛለህ፡፡ አምላኬ ሆይ በውበትህ የቀኑ ኮከብ ላይ ለማተኮር እንድታስችለኝና የልሳንህንም የወይን ጠጅ እንድታድለኝ፣ የስሞች ንጉስ በአደረግኽው በሰማይና በምድር ያሉት ሁሉ በተመሰጡበት ስምህ እማጠንሃለሁ፡፡ አምላኬ ሆይ፣ ፍጹም ቅዱሱን ፍጹም አንፀባራቂውን ፍጹም ኃያሉን ፍጹም ታላቁን ፍጹም የተከበረውንና ፍጹም ክብር የተመላውን ስምህን እንደያዝኩ፣ በዚህ ዓለምና በወዲያኛው ዓለም ያሉት ሁሉ በተንጠላጠሉበት የካባህ ዘርፍ ላይ ተንጠላጥዬ ታየኛለህ፡፡ አምላኬ ሆይ፣ ፈቃድህ ከሚጠላው ከማንኛውም ነገር እንድታርቀኝና እርሱ የአንተ ምልክቶች ጎሕ የሆነው ወደ አበራበት ደረጃ እንድታቀርበኝ፣ በመለኮታዊው ሎጥ ዛፍ መንኮሻኮሽና በስሞችህ መንግስት ውስጥ የልሳንህ ልዝብ ነፋሾች ድምጽ እማጠንሃለሁ፡፡ አምላኬ ሆይ፣ ፍጹም ቅዱሱን ፍጹም አንፀባራቂውን ፍጹም ኃያሉን ፍጹም ታላቁን ፍጹም የተከበረውን ፍጹም ክብር የተመላውን ስምህን እንደያዝኩ፣ በዚህ ዓለምና በወዲያኛው ዓለም ያሉት ሁሉ በተንጠላጠሉበት የካባህ ዘርፍ ላይ ተንጠላጥዬ ታየኛለህ፡፡ አምላኬ ሆይ፣ ፈቃድህ ከሚጠላው ከማንኛውም ነገር እንድታርቀኝና እርሱ የአንተ ምልክቶች ጎሕ የሆነው ወደ አበራበት ደረጃ እንድታቀርበኝ፣ በመለኮታዊው ሎጥ ዛፍ መንኮሻኮሽና በስሞችህ መንግስት ውስጥ የልሳንህ ልዝብ ነፋሾች ድምጽ እማጠንሃለሁ፡፡ አምላኬ ሆይ፣ ፍጹም ቅዱሱን፣ ፍጹም አንፀባራቂውን ፍጹም ኃያሉን ፍጹም ታላቁን ፍጹም የተከበረውንና ፍጹም ክብር የተመላውን ስምህን እንደያዝኩ፣ በዚህ ዓለምና በወዲያኛው ዓለም ያሉት ሁሉ በተንጠላጠሉበት የካባህ ዘርፍ ላይ ተንጠላጥዬ ታየኛለህ፡፡ አምላኬ ሆይ፣ በዕውቀትህ ማከማቻዎች ውስጥ የተደበቁትንና በጥበብህ ማስቀመጫዎች ውስጥ የተሸሸጉትን እንድትገልጥልኝ፣ በዚያ ከፈቃድህ አንደበት ከመውጣቱ ውቅያኖሶች እንዲተምሙ ነፋሶችም እንዲነፍሱ ፣ ፍሬዎችም እንዲገለጡ ዛፎችም እንዲበቅሉ፣ ያለፉት ደብዛዎች ሁሉ እንዲጠፉ ፣ ግርዶሾችም ሁሉ እንዲተረተሩ ፣ ለአንተም ያደሩት ወደማይጨቆነው የእነርሱ ጌታ ገጽታ ብርሃን እንዲለግሱ ባደረገው ፊደል እማጠንሃለሁ፣ አምላኬ ሆይ ፍጹም ቅዱሱን ፍጹም አንፀባራቂውን ፍጹም ኃያሉን ፍጹም ታላቁን ፍጹም የተከበረውንና ፍጹም ክብር የተመላውን ስምህን እንደያዝኩ፣ በዚህ ዓለምና በወዲያኛውም ዓለም ያሉት ሁሉ በተንጠላጠሉበት የካባህ ዘርፍ ላይ ተንጠላጥዬ ታየኛለህ፤ አምላኬ ሆይ በመጽሐፍህ ውስጥ አንተ ላወረድከውና በፈቃድህም ለተከሰተው ከበቁት ጋር እንድትቆጥረኝ፣ እንቅልፍን ከሕሩያንህና ከተወዳጆችህ አይኖች ባባረረው የፍቅርህ እሳት፣ ጎህ በሚቀድበትም ሰዓት በእነርሱ አንተን ማስታወስና ማወደስ እማጠንሃለሁ፡፡ አምላኬ ሆይ ፣ ፍጹም ቅዱሱን ፍጹም አንፀባራቂውን፣ ፍጹም ኃያሉን፣ ፍጹም ታላቁን፣ ፍጹም የተከበረውንና ፍጹም ክብር የተመላውን ስምህን እንደያዝኩ፣ በዚህ ዓለምና በወዲኛው ዓለም ያሉት ሁሉ በተንጠላጠሉበት የካባህ ዘርፍ ላይ ተንጠላጥዬ ታየኛለህ፡፡ አምላኬ ሆይ ፣ ለታማኖችህና ለሕሩያንህ የፃፍከውን ለኔም ፍጹም በተከበረው ብዕርህ እንድትጽፍልኝ ለአንተ የቀረቡት በትዕዛዝህ ጦሮች መወጋትን እንዲቀበሉ፣ ለአንተ ያደሩትም የጠላቶችህን ሰይፎች በመነግድህ እንዲጋፈጡ ባደረጋቸው በገጽህ ብርሃን እማጠንሃለሁ፡፡ አምላኬ ሆይ፣ ፍጹም ቅዱሱን ፍጹም አንፀባራቂውን ፍጹም ኃያሉን ፍጹም ታላቁን ፍጹም የተከበረውንና ፍጹም ክብር ተመላውን ስምህን እንደያዝኩ፣ በዚህ ዓለምና በወዲያኛው ዓለም ያሉት ሁሉ በተንጠላጠሉበት የካባህ ዘርፍ ላይ ተንጠላጥዬ ታየኛለህ፡፡ አምላኬ ሆይ፣ ወደ አንተ ለተመለሰው ለእያንዳንዱ ሰው፣ አንተ የያዝከውንም ፆም ላከበረው፣ በአንተ ፈቃድ ካልሆነ በቀር ለማናገሩትና ያላቸውንም ሁሉ በአንተ መንገድና ለአንተ ፍቅር ሲሉ ለሰውት ያዘዝከውን ካሳ እንድትጽፍለት፣ ያፍቃሪዎችህን ጥሪ፣ የእነዚያን አንተን የሚናፍቀቱትንም የኃዘን ድምጽ እነዚያ ወደ ቅርበትህ ለመግባት የታደሉት የሚያሰሙትንም ጩኽት እነዚያ ላንተ ያደሩት የሚያሰሙትንም ማቃሰት ባዳመጥህበትና በፀጋህና በቸርነትህ፣ የእነዚያን ተስፋቸውን በአንተ ላይ ያደረጉትን ሰዎች ምኞቶች በአሟላህበትና ፍላጎቶቻቸውንም በፈቀድክበት ስምህ፤ የይቅር ባይነትም ውቅያኖስ በፊትህ በተመመበትና የቸርነትህ ደመናዎች በአገልጋዮችህ ላይ በዘነቡበት ስምህ እማጠንሃለሁ፡፡ ጌታዬ ሆይ፣ እነዚያ ህግጋትህን አጥብቀው የያዙትና በመጽሐፍህ ውስጥ የደነገግህላቸውን ያከበሩት የፈፀሙትን በደል ትሰርዝላቸው ዘንድ በአንተው በራስህ በምልክቶችህ በግልጽ መታወቂያዎችህ በሚያበራው የውበትህ የቀኑ ኮከብ ብርሃንና በቅንጫፎችህ እማጠንሃለሁ፡፡ አምላኬ ሆይ ፍጹም ቅዱሱን ፍጹም አንፀባራቂውን ፍጹም ኃያሉን ፍጹም ታላቁን ፍጹም የተከበረውንና ፍጹም ክብር የተመላውን ስምህን እንደያዝኩ በዚህ ዓለምና በወዲያኛው ዓለም ያሉት ሁሉ በተንጠላጠሉበት የካባህ ዘርፍ ላይ ተንጠላጥዬ ታየኛለህ፤

በፆም ወይም በሌሎች የማለዳ ጊዜያት የሚደረግ አምላኬ ጌታዬ ሆይ! እኔ አገልጋይህ የአገልጋይህም ልጅ ነኝ፡፡ የአንድነትህ የቀኑ ኮከብ ከፈቃድህ ጎሕ በበራበትና በትዕዛዝህ መፃሕፍት ውስጥ በተደነገገው መሠረት ጮራውን በመላው ዓለም ላይ በፈነጠቀበት በዚህ ማለዳ ከመደቤ ነቅቻለሁ፡፡ አምላኬ ሆይ ወደ ዕውቀትህ ብርሃን ውበት ለመንቃት በመቻላችን ለአንተ ምስጋና ይድረስህ፡፡ ጌታዬ ሆይ አንተን በስተቀር ሌላውን ሁሉ ለመተው የሚያስችለንንና ከአንተ በስተቀር ከማንኛውም ቁራኛነት የሚያነፃንን ላክልን፡፡ በተጨማሪም ለእኔ ለእኔ ውድ ለሆኑትና ለዘመዶቼ፤ ለወንዱም ለሴቱም የዚህኛውንና የመጪውን ዓለም መልካም ነገር ሁሉ እዘዝልን፡፡ አቤቱ አንተ የመላው ፍጥረት ተወዳጅና የጠቅላላው ሁለንተን ዓለም ምኞት የሆንክ ሆይ፣ የእርኩሱ አንሾኳሻኪ መገለጫዎች ከአደረግሃቸው ከእነዚያ በሰዎች ልቦናዎች ከሚያንሾኳሹኩት፤ በማይቋረጠው ጠባቂነትህ ጠብቀን፡፡ አንተ የፈቀድከውን ለማድረግ የማይሳንህ ነህና፡፡ በእውነቱ አንተ ፍጹም ኃያሉ፤ በአደጋ ጊዜ ረዳቱ በገዛ ራሱም ነዋሪው ነህና ፡፡
ጌታ አምላኬ ሆይ ፤ እርሱን ከሁሉም በላቁት ስያሜዎችህ ላይ የሰየምከውን በእርሱም ፃድቃንን ከኃጢአን የለየህበትን ባርከው፣ እኛም አንተ የምትፈቅደውንና የምትወደውን እንድንሠራ በፀጋህ እርዳን፣ በተጨማሪም አምላኬ ሆይ የአንተ ቃላትና ፊደላት የሆኑትን ፊታቸውን ወደአንተ ያቀኑትን ወደአንተም ገጽታ የዞሩትን ጥሪህንም ያዳመጡትን ሁሉ ባርካቸው፤ በእውነቱ አንተ የሰዎች ሁሉ ጌታና ንጉሥ በሁሉም ነገሮች ላይየበላይ ነህ፡፡
ጌታ አምላኬ ሆይ፣ስምህ የተወደሰ ይሁን! ወደ አንተ ተመልሰው የአንተን እምነት ለረዱት አገልጋዮችህ ልቦቻቸውን የሚያስደስተውን ከምሕረትህ መንግስተ ሰማይና ፍቅር ከተመላበት የአንተ የርኅራኄ ደመናዎች እንድታዘንብላቸው፣ ሰዓቱ በደረሰበት፣ ትንሳኤውም በተፈፀመበት፣ ፍርሐትና መንቀጥቀጥም በእነዚያ በሰማይ በሚገኙት ሁሉ፣ በምድር ላይ በሚገኙትም ሁሉ ላይ በወረደበት ስምህ እማፀንሃለሁ፡፡ ጌታ ሆይ፣ ወንድ አገልጋዮችህንና ሴት አገልጋዮችህን ከእውነት የራቁ እምነቶችና የከንቱ አስተሳሰቦች ጦሮች ሊያደርሱባቸው ከሚችሉት አደጋዎች እንድትጠብቃቸው፣ ከፀጋህም እጆች በለዘብታ የሚወርዱትን የዕውቀትህን ውሃዎች መጠጥ እንድትሰጣቸው እለምንሃለሁ፡፡ አንተ በእውነቱ ፍጹም ኃያሉ፣ ከሁሉ በላይ የተከበረው ፣ ዘላለም ይቅር ባዩ፣ ከሁሉም በላይ ለጋሱ ነህና፡፡
እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ! የፍቅርህን ገመድ አጥብቄ በመያዝ፣ ራሴንም ሙሉ በሙሉ ለአንተ እንክብካቤና ለጥበቃህ በመስጠት ከቤቴ ወጥቻለሁ፡፡ ተወዳጆችህን ከእነዚያ ከትክክለኛው መንገድ ከራቁትና ከጠማማዎቹ፣ ከእያንዳንዱም አመፀኛ ጨቋኝ፤‹ ከእያንዳንዱም ከአንተ የራቀ ክፉ አድራጊ በጠበቅህበት ኃይልህ፣ እኔንም በቸርነትህና በፀጋህ ከማንኛውም አደጋ እንድትጠብቀኝ እማፀንሃለሁ፡፡ በስልጣንህና በኃያልነትህም በደህና ወደቤቴ ለመመለስ አስችለኝ፡፡ በእርግጥ አንተ ፍጹም ኃያሉ፣ በአደጋ ጊዜ ረዳቱ፣ በገዛ ራሱም ነዋሪው ነህና፡፡

*‹‹ዕለታዊ የግዴታ ፀሎቶች በቁጥር ሶስት ናቸው፡፡ ምዕመኑ ከእነዚህ ከሶስቱ ፀሎቶች የፈለገውን እንዱን ለመምረጥ ሙሉ በሙሉ ነፃ ነው፤ ግን ከእነዚህ አንዱን አብረውት በሚሄዱት መመሪያዎች መሠረት የመድገም ግዴታ አለበት፡፡

*የግዴታ ፀሎቶች ትህትናንና ታዛዥነትን የሚጋብዙና፣ ሰው ፊቱን ወደ እግዚአብሔር በመመለስ ለእርሱ ምሀላ እንዲያወርብ የሚረዱት በመሆናቸው በየዕለቱ መደገማቸው ግዴታ ነው፤ እንዲህ ባሉት ፀሎቶችም አማካይነት የሰው ልጅ ከእግዚአብሔር ጋር ግንኙነት ይፈጥራል፣ ወደ እርሱም ለመቅረብ ይሻል፣ ከእውነተኛ የልቡ ፍቅረኛም ጋር ይነጋገራል፣ እንዲሁም መንፈሳዊ ደረጃዎችን ይቀዳጃል፣

ይህ ፀሎት በየዕለቱ ከቀትር እስከ ፀሐይ መጥለቂያ ባለው ጊዜ ውስጥ አንዴ የሚደረግ ነው፤ አምላኬ ሆይ አንተን እንዳውቅና እንድሰግድልህ እንደፈጠርከኝ እመሰክራለሁ፡፡ በዚህች ሰዓት የእኔን ደካማነትና የአንተን ኃያልነት የእኔን ምስኪንነትና የአንተን ሀብታምነት አረጋግጣለሁ፡፡ ከአንተ በአደጋ ጊዜ ረዳት፣ በገዛ ራሱም ነዋሪ ከሆንከው በስተቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡