Selections from the Writings of the Báb

Amharic · Báb

BB00490 BB00490

Add range:
በስመ እግዚአብሔር በሚያርበደብደው ግርማ ጌታ በሁሉን አስገዳጁ! የገዢነት ምንጭ በእጁ ውስጥ ያለው ጌታ የተቀደሰ ይሁን፡፡ እርሱ “ሁን” ሲል በሚሆነው የትዕዛዝ ቃሉ የፈቀደውን ማንኛውንም ነገር ይፈጥራል የሥልጣን ኃይል ከዚህ በፊት የእርሱ ነበር፣ ለወደፊቱም የእርሱ መሆኑን ይቀጥላል፡፡ እርሱ የፈለገውን ማንኛውንም ሰው በትዕዛዙ ፍጹም ኃይል ድል አድራጊ ያደርገዋል፡፡ እርሱ በእውነቱ ኃይል የተመላው ፣ ፍጹም ኃይሉ ነው፡፡ በግልፀትና በፍጥረት ዓለማት በመካከላቸውም በሚገኘው በማንኛውም ውስጥ ክብርና ግርማ ሁሉ የእርሱ ናቸው፡፡ በእውነቱ እርሱ ምንም የማይሳነው፣ ንዑዱ ነው፤ ከእምቅድመ ዓለም ጀምሮ እርሱ የማይበገር ሃይል ምንጭ ነበር፡፡ በዚህም ሁኔታ ለዘለዓለም ይኖራል፡፡ እርሱ በእርግጥ ኃያልነትና የስልጣን ጌታ ነው፡፡ በሰማይና በምድር በመካከላቸውም የሚገኙት ዓለማት ሁሉ የአምላክ ናቸው፡፡ ስልጣኑም በሁሉም ነገሮች ላይ የላቀ የበላይ ነው፡፡ የምድርና የሰማይ ሀብት ሁሉ፣ በመካከላቸውም የሚገኙት ነገሮች ሁሉ የእርሱ ናቸው፡፡ ጥበቃውም በሁሉም ነገሮች ላይ ተዘርግቶ ይገኛል፡፡ እርሱ የሰማያጥና የምድር፣ በመካከላቸውም የሚገኝ የማንኛውም ነገር ፈጣሪ ነው፡፡ በእውነቱ እርሱ በሁሉ ነገሮች ላይ ምስክር ነው፡፡ እር በሰማያትና በምድር የሚኖሩትን፣ እንዲሁም በመካከላቸው የሚያገኙትን ሁሉ ስለሥራቸው የሚጠይቅ ጌታ ነው፤ በእውነቱ እግዚአብሔር ስለተሠሩት ስራዎች ለመጠየቅ ፈጣን ነው፡፡ እርሱ በሰማያትና በምድር በመካከላቸውም ለሚገኘው ሁሉ የተመደበውን ድርሻ መጠን ይወስናል፡፡ በእውነቱ እርሱ የላቀው ጠባቂ ነው፡፡ እርሱ የሰማይንና የምድርን በመካከላቸውም የሚገኘውን ነገር ሁሉ ቁልፎች በመዳፉ ውስጥ ይይዛል፡፡ እርሱ በገዛ ራሱ ፍላጎት፣ በራሱ ትዕዛዝ ስጦታዎችን ይሰጣል፡፡ በእርግጥ ፀጋው ሁሉን ያቅፋል፣ እንዲሁም እርሱ ሁሉን አዋቂው ነው፡፡ በል፤ እግዚአብሔር ለእኔ አርኪዬ ነው፣ እርሱ የሁሉንም ነገሮች ዓለም በመዳፉ ውስጥ የያዘው ነው፡፡ በሰማያትና በምድር በመካከላቸውም በሚገኙት የእርሱ ሠራዊት ኃይል፣ ከአገልጋዮቹ መካከል የፈለገውን ማንኛውንም ሰው ይጠብቃል፡፡ በእውነቱ እግዚአብሔር ሁሉንም ነገሮች ይጠብቃል፡፡ ጌታ ሆይ ለመገመት ከሚቻል በላይ የተከበርክ ነህ! በፊት ለፊታችንና ከበስተኋላችን፣ ከእራሶቻችን በላይ፣ ከበስተቀኛችን ከበስተግራችን ከእግሮቻችን በታችና በተጋለጥንበት በእያንዳንዱ ሌላ ጎን በኩል ከሚገኘው ከማንኛውም ነገር ጠብቀን፤ በእውነቱ አንተ ጥበቃ ከሁሉም ነገሮች ላይ አይቋረጥም፡፡

BB00619 BB00619

Add range:
  • For the Dead

እርሱ አምላክ ነው፤ እርሱ የፍቅራዊ ደግነትና የቸርነት ጌታ የሆነው የተከበረ ነው፤ አንተ ምንም የማይሳንህ ጌታ የሆንክ አምላኬ ሆይ፣ ክብር ለአንተ ይሁን፣ ምንም የማይሳንህ ስለመሆንህና ስለኃያልነትህ ስለሉዓላዊነትህና ስለፍቅራዊ ደግነትህ፣ ስለፀጋህና ስለሥልጣንህ፣ ስለሕያውነትህ አንድዬነትና ስለህላዌህ አንድነት፣ከፍጥረት ዓለምና በዚያም ከሚገኙት ሁሉ የተቀደስክና የተከበርክ ስለመሆንህ እመሠክራለሁ፡፡ አምላኬ ሆይ! ከአንተ በቀር ከሁሉም ተላቅቄ አንተን አጥብቄ መያዜንና ወደ ቸርነትህ ውቅያኖስ፣ ወደ ልግስናህ ሰማይና ወደ ፀጋህ ቀኑ ኮከብ ዛሬ ታየኛለህ፡፡ ጌታ ሆይ! በአገልጋይህ ውስጥ አደራህን እንዳስቀምጥክና ይህም ለዓለም ህይወት የሰጠህበት መንፈስ መሆኑን እመሰክራለሁ፡፡ በቀናትህ የፈፀመውን ሥራ ምሕረት በተመላበት ሁኔታ እንድትቀበለው በግልፀትህ ሉል ብርሃን እለምንሃለሁ፡፡ በመልካም ፈቃድህ ክብር እንዲጎናፀፍና በአንተ ተቀባይነት እንዲያጌጥ ፈቃድህ ይሁን፡፡ ጌታዬ ሆይ! አቤቱ አንተ የሰዎች ሁሉ ጌታ ሆይ! እኔ ራሴና የተፈጠሩት ነገሮች ሁሉ ስለ ኃያልነትህ እንመሰክራለን፤ ይህን ወደ አንተ ወደ መንግስተ ሰማያዊ ስፍራህ፣ ወደ ላቀው ገነትህና ወደ ቅርበትህ ማረፊያ ያረገውን መንፈስ ከአንተ ከራስህ እንዳታገልለው እለምንሃለሁ፡፡ አምላኬ ሆይ፣ አገልጋይህ ብዕር ሊገልፃቸው አንደበትም ሊያወሳቸው በማይችል መንግስተ ሰማያዊ ሥፍራዎች ውስጥ ከሕሩያንህ፣ ከቅዱሳንህና ከመልእክተኞችህ ጋር እንዲወዳጅ ፈቃድህ ይሁን፤ ጌታዬ ሆይ፤ በእውነቱ ምስኪኑ ወደ ሀብትህ መንግስት ባይተዋሩ በክልሎችህ ውስጥ ወዳለው መኖሪያ ቤቱ እርሱ በጣም የተጠማው ወደ በረከትህ መንግስተ ሰማያዊ ወንዝ ገሥግሷል፡፡ ጌታ ሆይ ከፀጋህ ማዕድና ከበረከትህ ችሮታ ድርሻውን አትንፈገው፤ አንተ በእውነቱ ፍጹም ኃያሉ፤ ፀጋ የተመላው ፍጹም በረከት የተመላው ነህና! አምላኬ ሆይ፣ አደራህ ወደ አንተ ተመልሷል፡፡ አሁን አቀባበል ላደረግህለት እንግዳህ ስጦታዎችህንና ችሮታዎችህን ከፀጋህም ዛፍ ፍሬዎች መለገሱ በምድርና በሰማይ የሚገኙ ግዛቶችህን ከከበበው ፀጋህና በረከትህ የሚጠበቅ ነው፤ አንተ የፈቀድከውን ለማድረግ ሥልጣን አለህ፤ ከአንተ ፀጋ ከተመላው ከሁሉም በላይ በረከት ከተመላው ከሩኅሩኁ ከለጋሱ ከይቅር ባዩ ከክቡሩ ከሁሉን አዋቂው በቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡ ጌታዬ ሆይ ሰዎች እንግዳቸውን እንዲያከብሩ እንዳዘዝካቸው እርሱ ወደ አንተ ያረገውም በእውነቱ አንተ ዘንድ እንደደረሰና ቅርበትህን እንደተቀዳጀ እመሠክራለሁ፤ እንደፀጋህና እንደቸርነትህ ተቀበለው፣ በክብርህ አገልጋዮችህን ካዘዝካቸው ተግባር ራስህም ወደ ኋላ እንደማትል፣ እርሱን በበረከትህ ገመድ ላይ የተንጠላጠለውንና ወደ ሀብትህ ጎሕ ያረገውን እንደማትነፍገው በእርግጥ አውቃለሁ፡፡ ከአንተ ከአንዱ ከአንደዬው ኃይል ከተመላው፣ ከሁሉን አዋቂው በረከት ከተመላው በቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡ ጌታ አምላኬ ሆይ፣ ክብር ለአንተ ይሁን! እርሱን በዘላለማዊ ሉዓላዊነትህ ኃይል ያከበርከውን አታዋርደው ወደ ዘለዓለማዊ መቅደስህ እንዲገባ ያደረግኽውንም ከአንተ እንዲርቅ አታድርገው፤ አምላኬ ሆይ፣ እርሱን አንተ በጌትነትህ ጥላ ሥር የከለልከውን ከአንተ መሸሻው የነበርከውን ከአንተ ዘንድ ታባርረዋለህና እርሱን አንተ ከፍ ያደረግኽውን ታዋርደዋለህን. ወይም እርሱን አንተን ለማሰታወስ ያስቻልከውን ትረሳዋለህን? አንተ የተከበርክ፣ እጅግ በጣም የተከበርክ ነህ! አንተ ከእምቅድመ ዓለም ጀምረህ የመላው ፍጥረት ንጉሥና ዋና አንቀሳቃሹ የነበርከው ነህ፣ ለዘላለምም የተፈጠሩት ነገሮች ሁሉ ጌታና ወሳኛቸው ሆነህ መኖርህን ትቀጥላለህ፤ አምላኬ ሆይ አንተ የተከበርክ ነህ ለአገልጋዮችህ ምሕረት መለገስን ብታቋርጥ ሌላ ማን ምሕረት ያደርግላቸዋል፡፡ አንተ ተወዳጆችህን ካልደረህ ፤ ሌላ ማን ሊራዳቸው ይችላል? አንተ የተከበርክ፣ ለመገመት ከሚቻል በላይ የተከበርክ ነህ! አንተ ለእውነተኝነትህ የተወደስክ ነህ፤ በአርግጥም እኛ ሁላችንም አንተን እናመልካለን፤ አንተ በፍርድህ ግልጽ ነህ፣በእውነትም እኛ ሁላችንም ለአንተ እንመሠክራለን አንተ በእርግጥ ለፀጋህ የተወደድህ ነህ፤ ከአንተ በአደጋ ጊዜ ረዳቱ፣ በገዛ ራሱ ነዋሪ ከሆንከው በስተቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡
አምላኬ ሆይ! አቤቱ አንተ ኃጢአትን ይቅር ባዩ ስጦታዎች ሰጪው ጭንቅንም አትፊው ሆይ! በእውነቱ ሥጋዊ ልብስን ጥለው ወደ መንፈሳዊው ዓለም ያረጉትን ሁሉ ኃጢአት ይቅር ትልላቸው ዘንድ እማፀንሃለሁ፡፡ ጌታዬ ሆይ ከኃጢአት ሁሉ አንፃቸው ኃዘናቸውን አስወግድላቸው፣ ጨለማውንም ወደ ብርሃን ለውጥላቸው፤ ወደ ተድላ ገነት እንዲገቡ አድርጋቸው ፍጹም ንጹህ በሆነው ውሃ እጠባቸው፤ ከሁሉም በላይ ከፍተኛ በሆነው ተራራ ላይ ያለውን ግርማህንም እንዲያዩ አድርጋቸው፤